Wednesday, May 30, 2012

የምን ምናምንቴ !!!!










እንዲህ ነው !
ስነ-ግጥም…የውበት ልቀት ነው
ስነ-ግጥም…….የሰው ልጅ አእምሮ ረቂቅ ውጤት ነው
ስነ-ግጥም …….የራሱ ፍጻሜ አላማ አለው
ስነ-ግጥም……….የስነ ጽሁፍ ፈርጥ ነው፡፡
               © © ©

         ለዚህ ነው በስነ-ግጥም የሰው ልጅ ስሜቱን የሚጭረው ነገር ሲያገኝ የሚያለቅስበት፤የሚስቅበት፤የሚከፋበት፤የሚዝነናበት፤ወዘተ………፡፡   እናም እንደቀልድ ከላይ የገጠምኳትን ግጥሜን ለረጅም ጊዜ ሳጥኔ ውስጥ ቆልፌ በቅርቡ ትንሳዬዋን አግኝታ ለአቅመ ንባብ ስትበቃ በርካታ ገጣሚያን ልብ ውስጥ ገብታ በራሳቸው እይታ የተሰማቸውን ለማለት የበቁት……….፡፡ መቼም ምን ያህል ልቤን አንደነካኝ ቃላት አይፈታውም ! ሁሉንም አመሰግናለሁ ፊት አውራሪ ገጣሚ ዮሃንስ ሞላ ትልቁን ቦታ ይይዛል ከዚህ በኋላም መሰል ግጥሞች ይቀጥላሉ…………እኛም እንጽፋለን !!!! ፡፡
                    © © ©
       ቦንቡን
ቦንቡን  ካልፈራኸው  ንቀል  ከእንብርቷ
ይቆም  ከመሰለህ  ውበት  መለከቷ
በሸንቃጣ  ወገብ  እንዲህ  ተሞናድላ
በእንጆሪ  ከንፈር  በረዶውን  ስላ
ደረቷ  ሚሳኤል  መያዙን  ሳታውቀው
በአይኗ  ወላፈን  ፍቅርህን  ሳትፈጀው
መሞትን  ከመረጥክ
ትግደልህ  ብያለሁ  እሷም  እንድትገልህ  አንተም  እንደመረጥክ …….

,
አርአያ መርቲ መተሃራ
አቤት ስልጣኔ
የጆሮ ተወዶ  ዘንድሮ  ጉድ ፈላ
ምንስ  የቀረ  አለ  ያልተባሳ  ገላ
ውበት ነው፣እብደት  ነው  ወይስ  ስልጣኔ
ይህው  ጉድ  አሳየኝ ዝቅ  ብሎ  አይኔ
እምብርት  ወግ  ደርሶት  ጉትቻ  አጠለቀ
ተገንጦ  በይፋ  ይህው  ፀሀይ  ሞቀ
ቦዲ  የተባለው  መላ  ቅጡ  የጠፋ
ጡቶቿን  አጋልጦ  ያሳያል  በይፋ
ሚኒ  ደሞ ተብሎ  ጣል  የተደረገው
ሀፍረተ  ስጋዋ ይህው  አጋለጠው።
"
እብደት  ነው  ውበት ነው  ወይስ  ስልጣኔ"  ብዬ ቋጥሬ  ካስቀመጥኳት  ግጥሜ ከማስታወሻዬ  ላይ  የተወሰደች  ነች።
         © © ©
እመቤት በየነ
ቦንቡን  ካልፈራኸው  ንቀል  ከእንብርቷ
ይቆም  ከመሰለህ  ውበት  መለከቷ
በሸንቃጣ  ወገብ  እንዲህ  ተሞናድላ
በእንጆሪ  ከንፈር  በረዶውን  ስላ
ደረቷ  ሚሳኤል  መያዙን  ሳታውቀው
በአይኗ  ወላፈን  ፍቅርህን  ሳትፈጀው
መሞትን  ከመረጥክ
ትግደልህ  ብያለሁ  እሷም  እንድትገልህ  አንተም እ ንደመረጥክ ……
               © © ©
አርአያ መርቲ መተሃራ
    (……………)
የረከሰ  ገላሽ  እሳት  የለበሰ
ተከፍቶ  የተሰጠ ለህዝብ  የደረሰ
ምን ያደርግልኛል  የአይን  ትራፊ
ይህን ገላ ይዘሽ  ይልቅ  ከፌቴ  ጥፊ
የቆንጆ  ቀፋፊ።
      © © ©
ቢንያም አንረሃም
እንዲህ  መገላለጥ  ግድግዳን  ተግኖ
ለሚወዱት  ብቻ  ለሌላው  ተከደኖ
መፈንዳት  መጋየት  ከአልጋ  ጦር ሜዳ
መዋኝት  መዘፈቅ  ከፍቅር  ባህር  ውስጥ  ማንም  ላይጎዳ
ነበረ  የሚያምረው  የኛ  ባህል  ወጉ
እነ ሃፍረት  የለሽ  ተወልደው ሳያደጉ
የእርቃን  ምሩቃን  እነ መረን  ጥጉ
   © © ©
ሰኢድ አካ ኮቻ
የሴት  ልጅ  ውበትዋ
የስዋ  ማነንትዋ
ይጎላል  ሲሸፈን
መላው  ደም  ግባትዋ
ግን  ደግሞ  ሲጋለጥ
የተደበቀው  ክብሯ
አንገትን  ያስደፋል
ሲታይ  ገመናዋ
  © © ©
ለኡል
ገልገሎ
ልጅቱ
ባለ ፎቶይቱ
ፈቃድ ሳትጠየቅ  በግጥም  ተከባ
በቃል  ተከሽና  በስንኝ ተውባ
ሺህ  ሰው  ተነባ
ራሷን  ስታገኘው….
ያስደስታት  ይሆን  ወይንስ  ታነባ???!!
         © © ©
ብቱካ(ኖወላዊት)
  እርቃን ስልጣኔ
ጡትም ገሀድ ወጣ - ከፊሉ ተገልጦ፣
ዕምብርት ተጎበኘ - በጉትቻ አጊጦ፣
ዕድሜ ጤና ሰጥቶት - ለትዝብት የቆየ፣
ምን አለ እንዳትሉ - ነገር ካልታየ!
              ©  ©  ©
        (ከእዮብ ብርሃነ)

No comments:

Post a Comment