Wednesday, June 6, 2012

እንባዋ


እንባዋ ቁ2
'ንባ እያማጉ
ከንፈር ከተበላ
ታድያ እንዴት
ሊሆን ነው
ከከንፈር ሚፈሰው
የማሩስ ወለላ....?፡፡
ሞንጫሪት
©©©
Mesert le

እንባዋ ቁ3
እናትክን ተመልከት…..
ሰርታ ጥራ ግራ
ሁሉን ልታስደስት
በገበታው ማጀት…..
        ወጡን ስትወጠውጥ
ሽሮ ስጋ አይደል…..
        ወጡን የሚያጣፍጥ
ስላወቁ ሴቶች……….ጨው ጠብ ካላለ
           ጥፍጥና ሽሮ እንደሌለ
ይህን ስላወቁ አይናችን……..
                እንዳይዞር ገመዱ ማሰሪያው
ወጥን በጨው ከንፈርን በንባ ' ነው  
      ወዳጄ ወንድ ሚታሰረው::
ያኔ ነው ጥፍጥናው
 አልያ አኞ ነው ታኝኮ ማይጥመው
እና    …..
እወቀው  የጅምርህ  ኑሮ
የፍቅርህ  እምነት  ነው
የሷነቷ  ፈትልህ  ነው
የዘመናት  ቱባ ::
© © ©
Arhay merti mekash

የፊደል ጨዋታ


የፊደል ጨዋታ ቁ 2
ካቡጊዳ ሰፈር ከኛው ከወንዛችን
የቀዳኀው ወይኑ ይጥም ለጆሮአችን
         ብለህ የተየብከው
የግጥም ገነት በር መክፈቻው ቁልፉ ነው….

….
ግና በኔ ሀሳብ ሚስቴ እንዳወቀች
….
ሞራልና ድጋፍ ሰቷል ከተባለች
ብላ ብላ
ከፊደል ተራ ወጥታ
......  ያረገችኝ  ለታ
መድረሻም  የለኝም  ከፊደል  ገበታ …..አቦ  ምርጥ ነው!!!
© © ©
አርአያ መርቲ መካሻ

የፊደል ጨዋታ ቁ 3

      
ምንም ባቷ ቢመስል በቅቤ የታሸ
አትራፊው  እሱ ነው  እንዳላየ  የሸሸ
        
መከራው  ብዙ ነው ሲወጡ  ተነክሮ
በኋላም ያመጣል  ፀፀትና  ሮሮ
            
ማን  ጥሩ  አተረፈ  ከከበር ቻቻ
ምነው በቀረብኝ  ኖሮ  ማለት ብቻ
           
ምን  ሲጨፍር  ቢያድር  መስሎት  ያለው  ደስታ
ብዙ  ነገር  ቢያደርግ  በመጠጥ  ሞቅታ
ትጠብቀዋለች  ፀፀት  በሩዋን  ከፍታ
ደሞ በተራዋ  ደስታ  በሯን  ዘግታ
ይሄ  ነው  ምላሼ  ለፊደል  ጨዋታ፡፡
© © ©
Mulex peace
ሁለታችሁንም ገጣሚያን አመሰግናለሁ እንዲህ ነው ስሜት በግጥም ሲገለጽ!!! ለዚህም ነው……………………….
        ስነ- ግጥም የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ብዙ የህይወት ጉዳዮችን የሚያነሳ የስነ ጽሁፍ ዘርፍ ነው፡፡እንዲሁም የሰው ልጅ ሰው ከሆነበት ቋንቋውን ኪነ -ጥበብ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ አኳያ ሲታይ መጀመርያ በድርሰት መልክ የተከሰተ የቋንቋ ጥበብ ነው፡፡
     እያናዳንዱ ግጥም ጣዕም አለው፡፡ ጣዕሙ የሚለየው ከስር በተጠቀሱት ቅመሞቹ ነው፡፡  የሃሳብ ምርጫ፤የስሜቱ ንዝረት፤ንረት፤ግለት፤መንተግተግ፤አዲስነት፤በቋንቋው ጥራትና ምጥቀት፤ቀላልነት በሃረጋቱ ምጣኔ፤በዜማዊነት፤በትኩስነት በአጠቃላይ በቅርጹ በይዘቱ ይወሰናል፡፡