Thursday, May 24, 2012

ልምሰል የሞላለት


ልምሰል የሞላለት
አዎ "ልምሰል የሞላለት ! "
በልቸ ጠጥቸ ስለኖርኩ በድሎት i
መብቴ ተገፎ አጥቼ ነጻነት
በስደት ሃበሳ ስኖር ስንከራተት፤
የደላኝ ይመስላል ! አኗኗሬን ሲቃኙት፤
የደላኝ ይመስላል ! ተክለ ቁመናየን መላብሴን ሲያዩት፤
የደላኝ ይመስላል! ስናገር ሲያደምጡኝ የምኖር በስኬት !
ታዲያሳ. . . !
በአደባባይ ልሳቅ ከቶ ምን አለበት
በደስታ ልምነሽነሽ ልምሰል የሞላለት
ኑሮ ግብግቡን አስተውለው ሲያዩት፤
ድብብቆሽ ኑሮ፤ አለፋውን ስቅየት
የመንገዱን ርቀት የሰው ልጅን ክፋት፤
ሲታዘቡት ውለው ሲያሰላስሉ ቢያድሩት፤
ምስለኔያችን ከፍቶ ሲደሰኩት ኩሸት፤
ሰብዕና ጠፍቶ ሰው ሁሉ ሲራኮት፤
ወገኔ ዝም ብሏል ቤቱ እስኪደርስበት፤
ደፋር ይናገራል እሱ ምናለበት
"
እድል እጣቸው ነው የተፈጠሩበት"
"
ለምን መጡ" ይላል መድገፉ ጠፍቶት፤
ይለናል ጎረምሳው መደገፉ ጠፍቶት
ድምጽ ማሰማቱ ፤ውሃ ማቅረብ ገዶት
እናም. . .
ስላየሁ በአይኖቸ ይህን መሳይ ትንግርት፤
ስላየሁ ህይዎቱን የዳፋ ቀማሹ የመሪሩን ስደት፤
ያስታግሰው እንደሁ የንዳድ ቃጠሎ የብሽቀቴን ብርታት፤
ድብቅ ሽሽግ ብየ . . .ሲለኝ አለቅሳለሁ ለመረረው ህይዎት፤
አዎእውነት ብለሃል ወንድም አደም
ይህ ነው የእውነቱ ገጽታ የዚህች አለም . . .
"
በጨለውማ ተስፋ ፤ጥርሴ ጧፍ ከሆነ
የህይዎቴን ግርዶሽ ገላልጦት ካደረ፤
ምናለ ልሳቀው ባንች ሆየ ቅኝት
ልንከትከት በዜማ ልምሰል የሞላለት !"
                     ©  ©  ©
        ወዳጀ አደም ሁሴን ዘራፍ አስባልከኝ እኮ ) ! ግጥም ደስ ይላል . . . የላክልኝ ግጥም ውስጤን ነካችውና ከተጋደምኩበት ይህችኑ ቋጠርኩልህ ! ስንኝ መገጣጠሙን በትክክል አሳክቸዋለሁ ባልልም ስሜቴን ካስረዳልኝ ይበቃል! ገጣሚ አይደለሁ እንዳንተ ! ለሁሉም ይህችም ላንተ ትሆን ዘንድ ፈቅጃለሁ !
ነቢዩ ሲራክ

4 comments:

  1. ወዳጄ አደም እንዴት አሳምረህ በ ተዋቡ ቃላት ጥበብ በሚዘሩ እጆችህ ኣሳምረህ ልብ የሚነኩ ሃቅ የተሞላበት ስንኝ ቛጠሮ ነው ከልብ አመስግናለሁ

    ReplyDelete
  2. Magnificent poem! Shukren Mr. Adem

    ReplyDelete
  3. ኣዎ ልምሰል የሞላለት
    በጆሮየ ደጃፍ ትዝታ ልሰማበት
    ልብን የሚያቃጥል ኣንጀትን የሚያነድ
    ጆሮየ እየሰማ ባኣይኔም ሲንጎዳጎድ
    እኔ በሠራሁት ሌላ ሲሾምበት
    እኔ በጋገርኩት ጎራሽ ሲለቁበት
    ኣዎ ልምሰል የሞላለት
    በኣርተፊሻል ጥርሴ ሳቄን ላሳይበት

    ReplyDelete