ፍቅር ከራስ ወደድነት የነጻ ነው! ፍቅር ድንበር ዘለል ሀይማኖት አያውቅም !ፍቅር ጠረን ነው፤መላመድ ነው ! ፡፡ ይሄ አባባል አዲስ ላይሆን ይችላል ፡፡
ትላንት አንድ እጅግ በጣም ደስ የሚል የጋብቻ ስነ ስርአት ላይ
ተገኝቼ ነበር፡፡ ሙሽሪት ዘመድ ናት የአጎቴ ልጅ…….እጅግ ውብ ናት ለምን የሞዴል ስራ እንደማትሰራአይገባኝም ወይም መንገዱን አላገኘቺም…..ማለቴ
ተክለ አቋሟ የዛን መሰረት ያሟላ ይመስለኛል……ዛሬ ላይ የእርሻ ሰራተኛ ሆና አፈር ትቆፍራለች፡፡
ሰርጉ እየተካሄደ ነው ብዙ እድምተኛ ተገኝቷል ገምት ብትሉኝ ከ200 ነላይ
ይሆናሉ ወደ 15 የሚሆኑት የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው ምክንያት ሙሽራው የውጭ ሃገር ዜጋ በመሆኑ
# ትወዳታለህ ወይ ? ;
አልኩት የሞኝ በሚመስል ጥያቄ
# በጣም እንጂ በጣም ;
ቃላቶች እያጠሩት መለሰልኝ
# ያገባኋት እኮ ብወዳት ነው ; አለኝ አከለና
# ማለቴ ሃይማኖት ባህል ችግር አይፈጥርም ? ;
# ይገርምሃል ይሄን አስቤው አላውቅም ; አለኝና እሩቅ ተጓዘ በሃሳብ….. ጨመረናም
# በቃ በጣም እወዳታለሁ የህይወቴ አጋር እንድትሆነኝ ፈቅጃለሁ
;
ወደ ድግሱ ፊቱን መለሰ …..ሁለታችንም በኛ ባልሆነ ቋንቋ በተሰባበረ
እንግሊዘኛ ነበር የምናወራው እሱ ጀርመን እኔ ሃበሻ…… ፡፡ በድግሱ መጨረሻ ላይ ከታዳሚዎች ፤ከጓደኛ ፤ከመስሪያ ቤት ባልደረቦች፤
የስጦታ የመልካም መግለጫ ጋርድ እየተበረከተ ነው፡፡ ድንገት ባነንኩ ለካ ስጦታ መስጠት ነበረብኝ በጣም ተሰማኝ ፡፡ እንደቀል ግን
በሞባይ ፎቶ አነሳቸው ነበር ከዛም አልፎ ከሙሽራው ጋር በነበረን ቆይታ አንድ ነገር ልቤ ውስጥ ቀረ ……እናም ሙሽራውን እያሰብኩ
ይህች ግጥም ጻፍኩ ወይም ተወለደች እናም ስጦታ ትሆነኝ ዘንድ ሰጠኋቸው፡፡
No comments:
Post a Comment