Friday, May 4, 2012

ነፍሴ ገዳም ግቢ


          የደራሲና ጋዜጠኛ በአሉ ግርማን የህይወት ታሪክ ስናወጋ የመጨረሻ መጽሃፉ በሆነው በ #ኦሮማይ; ዙርያ በስሜት ተጨዋውተን እንደነበር ላስታውስ…….፡፡ አዎ በተለይ ደራሲው ይህን የመጨረሻ የሆነውን ልብ-ወለድ መጽሃፍ ሲጽፍ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችልና በመጽሃፉ ደስተኛ ያልሆኑ በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ባለስልጣኖች እንደነበሩ ጠርጥሯል……ወይም ያውቅ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ የስራና የእውቀት ጓደኞቹ በተለያየ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስነብበውናል፡፡ ይህንን ህይወቱን ዋጋ ያስከፈለውን መጽሃፉን ከመጻፉ በፊት በተለያዩ ጊዜ በሚሰጣቸው መግለጫዎች ወይም በሚያገኛቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ጽኑ እምነቱን፤አንድ ደራሲና ጋዜጠኛ ምን ማድረግ እንዳለበትና የሚጠበቅበትን እንዲህ ሲል መናገሩን ማንበቤን አስታውሳለሁ……፡፡ # ድፍረት የሌላት ብዕር ወረቀት ባታበላሽ ይመረጣል…..! ከአድር ባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ብዙ ያናገራል ! ; ይለናል…..፡፡
    ይህ እንግዲህ የደራሲውን ድፍረትና ለቆመለት አላማ ታማኝ መሆኑን……! እንጽፋለን ለምንልና ለምናስብ……. እውነተኛ ብዕር ምንጊዜም ከመቃብር በላይ ሊያስቀምጥ እንደሚችል አስተምሮን አልፏል፡፡ በዚህ መሃል ፊያሜታ አለች…..፡፡ መቼም በኦሮማይ መጽሃፍ ውስጥ ስሜቱን የሚተነፍስባትና መሪ ገጸ ባህሪው ስለሆነችው ፊያሜታ አውርቼ እንደማልጠግብ እያሳበቀብኝ መሆኑ ይገባኛል……!፡፡ በኔ ብቻ የሚቆም ግን አልመሰለኝም፡፡ አንድ ወቅት የጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዩ ገ/አብ # የጋዜጠኛው ማስታወሻ ; ሳነብ እንዲህ የሚል አነበብኩ፡፡
                          ©  ©  ©
      # # ኦሮማይ ; ን መጽሃፍ መርቄ ከከፈትኩ በኋላ በግብዣው ስነ ስርዓት ወቅት በመጪው የስነ-ጽሁፍ ህይወቴ ላይ አብይ ሚና የተጫወተው ገጣሚና ደራሲ አበራ ለማ ጋርም ለመተዋወቅ በቅቻለሁ፡፡ በዘመነ ደርግ አበራ ለማ የኦሮማይ ገጸ-ባህሪ ለሆነቺው ፊያሜታ የቋጠራትን #ፊያሜታ እምባባ; የተሰኘቺው ግጥምም ከኦሮማይ መጽሃፍ ጋር በዚያኑ እለት ነጻ የወጣች ሲሆን በወረሃ መስከረም 1984 ዓም ግጥሟ የዛሬይቱ ጋዜጣ ላይ ታትማለች ፡፡ ጥቂት ስንኞች ልቀንጭብላቹ ; ይለናን፡፡
እነሆ እናንተም ግጥሟን ተቋደሱልኝ….
ፊያሜታ፡- የጋዜጠኛ ማስታወሻ
         የጋዜጠኛ መተንፈሻ
ልብሽ በነ ሰውየው ሴራ ሲንገላታ
ፍቅር መች ሆኖ ፊያሜታ
የልብ አፍቃሪ ካገኘው ላይረታ
ፊያሜታ፡- ሰው እንጂ ፍቅር ምን ገዶት
እውር መባሉ በቀተረው ተሲያት
ባምባሽ በቀበሌሽ ልብ ታወረ
ብርሃን ፈልጎ ጀንበርን ጫረ
አንቺ ጽብቅቲ የሰሜን ዋልታ ጮራ
የታሪኩ እምብርት መቋጠርያ የበአሉ ደመራ!፡፡
         ©   ©   ©
ገጽ 120-121

No comments:

Post a Comment