Thursday, May 24, 2012

አውራ ዶሮ ለሁሉም !



እንዲህ ነው !
ስነ-ግጥም…የውበት ልቀት ነው
ስነ-ግጥም…….የሰው ልጅ አእምሮ ረቂቅ ውጤት ነው
ስነ-ግጥም …….የራሱ ፍጻሜ አላማ አለው
ስነ-ግጥም……….የስነ ጽሁፍ ፈርጥ ነው፡፡
               © © ©
                       አኩኩሉ……..
         ለዚህ ነው በስነ-ግጥም የሰው ልጅ ስሜቱን የሚጭረው ነገር ሲያገኝ የሚያለቅስበት፤የሚስቅበት፤የሚከፋበት፤የሚዝነናበት፤ወዘተ………፡፡   እናም እንደቀልድ ከላይ የገጠምኳትን ግጥሜን ለረጅም ጊዜ ሳጥኔ ውስጥ ቆልፌ በቅርቡ ትንሳዬዋን አግኝታ ለአቅመ ንባብ ስትበቃ በርካታ ገጣሚያን ልብ ውስጥ ገብታ በራሳቸው እይታ የተሰማቸውን ለማለት የበቁት……….፡፡ መቼም ምን ያህል ልቤን አንደነካኝ ቃላት አይፈታውም ! ሁሉንም አመሰግናለሁ ፊት አውራሪ ገጣሚ ዮሃንስ ሞላ ትልቁን ቦታ ይይዛል ከዚህ በኋላም መሰል ግጥሞች ይቀጥላሉ…………እኛም እንጽፋለን !!!! ፡፡
ጨዋታ 1
ላረባት ዶሮ ገዝቼ፣
ይጠቅማልቢሉኝ ሰምቼ፣
ፈልፍይ ብዬ ባስታቅፋት፣
እሷ ወር አለፋት
ለምን? ብዬ ባስጠይቃት፣
ነፋስ ነው አለች ያጠቃት፣
___
የሰፈራት
እኔ ግሙን ታቅፌ፣
ዘር አምጣአለች በመርፌ፤
አውራ ጠፋ አሉ ገሩ፣
ኩኩሉሚል በመንደሩ።
/
አደም ሁሴን/
ሰኔ 1/1997

ጨዋታ 2
አውራማ
ነበር ባገሩ፣
ግን ችግሩ...
ልቡ ሸሽቶ ከመንደሩ፣
መስፈር ጀምሮ ከዱሩ፣
እየመከነበት ዘሩ...
መሸ ነጋ መደንበሩ።
እንዲህም ቢሆን ነገሩ፣
እኛን የጎዳን - መብረሩ፤
ግሙን ታቅፎ መኖሩ።
    © © ©
/
ዮሐንስ ሞላ/
ግንቦት 15/2004
አውራ ጠፋ ኡኡታ
አውራ ጠፋ ኡ ኡ ታ
በርበሬ
 
ቀንጥሱ  ድንፋታ
ችግሩ  በተባዕት  መች ይፈታ
እንስትስ  መቼ  አረባችሁ
ጥሩ  አውራ  እሚተካላችሁ
    © © ©
ኤርሚያስ ሙሉ
ኤዲያ !.....
ምን አውራ አለና ነው
==አውራ ጠፍቶ ባገሩ:
ስያስካካ የሚውለው
==ሴቱ ሆንዋል በመንደሩ:
አውራማ ድሮ ቀረ
==ያውም አውራ ቢሉ አውራ ዶሮ:
ለጎረቤት የሚተርፍ
==የመንደሩን አስፈልፍሎ:
እንግዲህ ቄቦች ሁሉ
==ምን ይውጣችሁ ይሆን:
ዝምብለው ቢታቀፉት
==ያላውራ ጫጩት አይሆን::
         © © ©
ብቤን ከበደ
esus neber bayiseber
keandwa sikenif keandwa siber
biyakit enji madaresu
wegu endayiker yelet misu
አንዱአለም መኮንን
doros ale awira doro  ዶሮስ አለ አውራ ዶሮ
yeteshale kezendiro  
የተሻለ ከዘንድሮ
chiro yemiyadir yemayidekim  
ጭሮ የሚያድር የማይደክም
serto asdesach yemayilegim  
ሰርቶ አስደሳች የማይለግም
tardo enji cherisewit  
ታርዶ እንጂ ጨርሰውት
lemasfelfel demo chachut  
ለማስፈልፈል ደግሞ ጫጩት
gorded gorded kinfun zerga  
ገርደስ ገርደስ ክንፉን ዘርጋ
geref germem eyalaga
ገ ረፍ ገርመም እያለ
kebuu hula sishkoremem  
ከቡ ሁላ ሲያሽኮረምም
bilo shulik anigegnim  
ብሎ ሹልክ አንገናኝም
አንዱአለም መኮንን
የብሌንን ታሳቢ አድርጌ ጨዋታ 4 ልበለው?
ከአህያና ፈረስ በቅሎን ላበቀላት
የቅይጥ የክልስ የእንግዳ ዘር ጠላት
ይቺ ዶሮ የሚሏት
ከዘሯም እንዲህ ናት
ያላ'ውራ አይሆንላት!
ሲባል ሰማና
አውራ የተባለ፤ ድንጉላ ደፈራት!

'
ቢሸግር እኮ ነው' አለ ትግሬ፤ ሃሃሃ
          ©  ©  ©
ምኪን ፑር
አውራ ጠፋ አትበለኝ
ቆፋፍሬ
መሬት ጭሬ
ልበላ……
ሆዴን  ልሞላ።
ስውተረተር
ስግተረተር
ሳውካካ
ሳስካካ
ክንፌን  አራግፌ
ባጠገቧ  አልፌ
ሴቷንም  ጎሽሜ
አሳስቄ  ስሜ።
እንዲህ  እንደደላኝ
ብታየኝ  አምሮብኝ
እጅግ  ቀናህብኝ
ተንኮል  ዘየድክብኝ።
ይታረድ  ተባለ  ቢላዋ  ተሳለ
ውሃ  ተቀቅሎ  ሽንኩርትም  በሰለ።
እናም...
ቢላዋ  እንደ  ሃብል  ካንገቴ  አልብሰኸኝ
ዘሬን  እያጠፋህ  አውራ  ጠፋ  አትበለኝ።
      © © ©
ዳዊት ኪንግ
አውራ ጠፋ ኡኡታ
አውራ  ጠፋ  ኡኡታ
በርበሬ
 ቀንጥሱ  ድንፋታ
ችግሩ  በተባዕት መች ይፈታ
እንስትስ  መቼ  አረባችሁ
ጥሩ  አውራ  እሚተካላችሁ::
    © © ©
ኤርሚያስ ሙሉ
ዴቭ አልተቻልክም
ግን ምክንያት አይህንም
ዝንተ  አለም  መሞንጨር
አትሞክር  ለመብረር
አለምን  ለመዞር
እዛው  አንድ  ቦታ
ስትጭር  ስትሞ ነጨር
ከውደ ኋላ  መጥተው
በአፍጢምህ  ፍንጭር
   © © ©
ኤልሳ ተገኔ
አውሉማ   አውራ ዶሮ
ሴቱን  አስከትሎ  ሲያበላ  ነው  መሬት ጭሮ
መክቷት  ከሌላ  ከብሮ  አስከብሮ
ተፋልሞ  ታግሎ
ጥሎ  ወይ  አስጥሎ
ወንድነቱን  አስመስክሮ
ዘሩን  ሊተካ  አስፈልፍሎ
ባይሆን  እንኳ
ሰፈር  መንደሩን  ካላስከበረ  ሆኖ  ታዳሚ
እሱን  ብሎ  አውራ ዶሮ
የትምሂያጅ  ነው  ለቃቃሚ::
   © © ©
መርከብ ብርሃኑ
ዶሮ  እሮሮ
ሊያደነቁር  ጆሮ
ላያመጣ  ለውጥ
ከጭልፊት  ላያስመልጥ
መጮህ  ማቅራራት
ሚስቱን  ሊሽወዳት
አለለሁልሽ  ሊላት
ግን  ምን  ያደርጋል ......!!!
ሲመጣ  ቁርጡ ቀን
የቢላ  ራት  ሊኮን
አያስጥል  ጩኸት
አፍ  ከፍቶ  ማዛጋት
   © © ©

ልዑል 24may
ገልገሎ አርቲሎ
ጆን ምርጥ ጨወታ
 በስንት ግዤ ግድግዳዬ ላይ መጣ )
ያሬድ ሽፍራው ፍልፍሉ
ድሮ ነው አሉ ሰውየው ከፍርሃቱ የተነሳ በምሽት ብቻን እንዳይወጣ ሚስጡን ደጅ ቁሚልኝ ይላታል ……በኋላ ለእናት አገር ጥሪ ካልዘመትኩ ሲል ሚስቲቱ እንዲህ ስትል መለሰችዘመቻው ቀርቶብኝ ደጅ በሸናህልኝአስከትላም ይህን ተረከች
አውራዶሮ - ስጭኝ ስጭኝ ዱላውን እለዋለሁ ናላውን
ሴት ዶሮ - አንቱማ አንቱማ አትዋሹ አጥር ለአጥር ልትሸሹ
አውራዶ፡- እንዳም እንዲያም ስላልኩሽ ዕንቅቡን ድፊብኝ እባክሽ…….. ያምራል ያምራል በርታ
ሳራ በላይነህ
እስቲ መልሱልኝ
--አውራ አለ የምትሉ:
ተሰደው እያያችሁ
--
ሴት ዶሮዎች ሁሉ
ለፍቶና ጫጭሮ
--
አኩኩሉ ብሎ
'
ነይ እንብላ' ቢላት
--
ያለውን ተካፍሎ
በዶሮኛ ቕንቕኣ
--
አለሁልሽ ቢላት
መች ትሰደዳለች
--
አለኝታ ቢሆናት::

አንተን ብሎ አውራ
--'
አውራ' ነኝ ምትለው
ጭሮ ሚያበላቸው
--
ቄቦችህ አውራ አተው
የባእድ አውራ ሲሳይ
--
ሆነው የሌላ አውራ
አያሳፍርህም
--
አሁን ስታቅራራ ?
        © © ©
ብሌን ከበደ
እኛን  ምን  ሊጎዳን  መብረሩ
እዘን  ለሱና  መንደሩ፤
ሲለው  ምጥቶ  ለሚኖረው
ግሙን  ለቀሪው  አሳቅፎ  ሊያኖረው፤
አውራው
ተው  ብሎ  አያስቀርው
ሲበር  ዝም  ብሎ  ሲቨኘው
ሲምጣ  ሲቀበለው
ግሙም  ለሱ  ተረፈው
መንደሩማ  መንደር ነው፤

ቹቹ 16 2004
ያለው ማማሩ
የሌለው መደበሩ
አለች ቄብ ዶሮ
ኩኩሉ ብሎ
የሚጮህላት
ብታጣ ደራሽ ቶሎ
አውራ ሆኖ ይሚያኖራት
የኩራት ዘውድ ሚደፋላት
ምን አውራ አለ ዘንድሮ
ሁሉም አግዳሚ ላይ ተደርድሮ
ቆቅ በቻ እንጂ ዛሬ ያለው
አካውንቱን የሚለይው
ዶሮ የለ አውራ ዶሮ
የሚያኖርሽ አንቀባሮ
ሁሉም ቆቅ ነው
ማይበላ ማያስበላ
አምስት ሳንቲም የማይደማው
    © © ©
  ኤልሳ ተገኝ

2 comments:

  1. ኩኩሉ ባዪል በማለዳ
    ስልክዋ አላርም እያላት መቼ ልትጎዳ
    መች ፈለገች አሳዳሪ
    ቀላቢ ሰፋሪ
    የተሰጣ እህል ከደጅ መቸ ጠፍቶ
    ስንዴ ገብሱ ሽሮው ፀሃይ ሊሞቅ ወጥቶ
    ከበርሜሉ ተጠግታ
    ለዉሃ ጥም ለጠብታ
    ለከተሜ ዶሮ እንዲህ ያልፋል ቀንዋ
    መሸትሸት እስከሚል እስክትወጣ ቆጥዋ
    ብርድ ብርድ እስኪላት እስኪመጣ እንቅልፍዋ
    ጥምን ከሚያረካው
    ሆድን ከሚሞላው
    ጸሃይ ከሚሞቀው ሽሮ
    እስዋን የናፈቃት - ምስኪን አውራ ዶሮ

    (ከአሞራው ዘ-ጉለሌ፡ ለልጅ አደም ሁሴን ድህረ ገፅ የታሰበች ትንሽ ግጥመ በረከት)Auguest 2012, London

    ReplyDelete