ሽቦ ጊቢ
ጊዜው እንዴት ይሮጣል……..ገምት ብትሉኝ አንድ ሀያ አመት አካባቢ ይሆነዋል፡፡
የአንድ ሰፈር የአንድ አካባቢ ልጆች ነን ደስ የሚል ጣፋጭ ጊዜ አሳልፈናል….የማይረሳ፤ፍቅር የተሞላበት ተናፋቂ ጊዜ…….. አሁን
የሆነ ያህል እንደ አዲስ ይሰማኛል፡፡ በዘር ፤በቀለም ፤በሃይማኖት ፤በጎሳ በጥቅም ያልተከፋፈለ ንጹህ ፍቅር ያለበት…….፡፡ እንግዲህ
ፌስ ቡክ (ፈቅጄ በገባሁ) ብየዋለሁ አንዱ አብሮ አደጌ የፎቶ አልበም ውስጥ አገኘሁት…… እጅግ ልቤ ተነካ በትዝታ እሩቅ ተጓኩ……በቀላሉ
ተፈጥሮን ለማድነቅ የተለያየ ቦታ እንሄዳለን፤እንዝናናለን፤እንስቃለን፤እንደንሳለን፤እንጨፍራለን፤ ክፋት የለም ፤ምቀኝነት አይታሰብም፤ደግነት
ግን በትልቅ ዙፋን ላይ ተደላድሎ የነገሰበት ወርቅ ጊዜ……..(ይሄ በሁሉም በወቅቱ የነበረ የሃገሬን ወጣትነት የህይወት ዘመን ይወክላል)፡፡
ዛሬ ሁሉም ተበታትኗል ፎቶውን ሲያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን ?????፡፡
ስማቸውን
ለማስታወስ ልሞክር (ቢንያም አለሙ፤ፍሬ ወይኒ፤ራሄል ተከስተ፤ትዕግስት(ሚጢጢ)ንጉሴ፤ተዎድሮስ ካሳሁን፤መስከረም ተከስተ፤ያሬድ ካሳሁን፤አማን
ረዘነ፤ቆንጂት ሁሴን፤ዮሃንስ አሸብር፤ሰለሞን ተከስተ፤ስንታየሁ ካሳሁን፤ኢሳያስ ዮሴፍ፤አደም ሁሴን፤አራዶም ሰለሞን፤ሮቤል ረዘነ፤ዽጥሮስ
ዳዊት፤ኤዴማ ሂዲ፤ቴዎድሮስ በየነ) እነሆ በረከት ብለናል፡፡
የበረሃዋ ገነት
ከወደ ምስራቅ ጸሀይ መውጫ
ያ'ድማስ ጮራ ህብር መገለጫ
ያላፊ አግዳሚው ፍኖት መሳለጫ
የከረዩ ውበት ያ..ክምክም ጎፈሬ
የኢቱ የአፋር ካፎት የሻጠው ጊሌ
የብሄር ስብጥር የግራር ዛፍ ፍሬ
ከበረሃ መሀል ያለሽው መንደሬ
የ'ትብቴ ማረፍያ እልፍ ዓለም ክትሬ
ከፈንታሌ ጋራ ካ’ዋሽ ወድያ ማዶ
ህብረት እንደ ማገር በፍቅርሽ ተገምዶ
የእህል ውሀ ነገር ካድማስ ወድያ ማዶ
ልቤን ካንቺው ትቼ አካሌ ተሰዶ
ፈገግታ§ን ውÂ ደስታው ከኔ ርቆ
ድንገት ከሳሎኔ ከመስታወት ቆሜ
ጥርሴ ላይ የቀረ ያኖርሺው ማተቤ
ተገልጦ የማያልቅ የህይወት አልበሜ
የማንነት ድርሳን መለያ ቀለሜ
ተዳፍኖ ያለውን የልጅነት ህልሜን
ከፍቼው ልተርክ የትዝታን ኪዳን
ጨልፌው ለመጋት ጥሜን ለአመሌ
ብእር ጦሬን ሰበኩ ዝምታን ሰብሬ፡፡
ከስንኝ ቋጥሬ ቃላት ብዘራልሽ
አደባባይ መሐል ማ‘ሌት ብቆምልሽ
መርቲ መተሐራ
አንቺ ገነት የበረሀ
የመቻቻል ባህል የመኖር ስንክሳር
የሰርቶ ማደግን ካሰቡት
የማደር
የእንግዳ አቀባበል መልካም ስነምግባር
እንደ ፈንታሌ ጋራ ዙርያሽ ገዝፎ
ያለ ከልካይ ባዋጅ አየር ላይ ተንሳፎ
አዋሽ ሆደ ቡቡ አዋሽ ዝምተኛ
አዋሽ ሁላ ሁሉ አዋሽ ሚስጥረኛ
አዋሽ አይታክቴ ምድርሽን ሰንጥቆ
የተጠማን ገላ አንጀት ሆድ አርሶ
አፈርሽን ረስርሶ
በእድገት ላይ ጸጋ ውበትሽን ጨምሮ
ወዛደርሽ ወዙን ሳይቆጥብ ገብሮ
ነገውን በተስፋ በሙዳዩ ቋጥሮ
ፍቅር ሲያስተሳስር ሰግሮ
ዘመን ዘመን ተካ ባ'ንድነት ጠንክሮ፡፡
መርቲ መተሐራ
አንቺ ገነት የበረሀ
የአድባር ከራማሽ ቆሌ
ከጂንፉ ጋራ እስከ ፈንታሌ
ከአባድር እስከ ጮሬ
የለምለም ቄጤማው የአዕዋፋት ዝማሬ
ከበሰቃው ማዶ
ውበትሽ አፍ ገዝቶ
ሲናገር ሰማሁት
ፍቅር ጉልበት ሆኖት፡፡
መርቲ መተሐራ
አንቺ ገነት የበረሀ
ከሙቀትሽ ሞቀን
በንፍጦ ግንፍሌ
ከወንዝሽ ቦጭርቀን
ከመስክሽ ፈንጥዘን
ከስኳርሽ ልሰን
ሸንኮራሽን ግጠን
ስንፈልግ ተጣልተን
ያለ ሽማግሌ ከዋርካው ስር ታርቀን
አሳድገሽናል በመቻቻል ሪቫን
በፍቅርሽ ተቋጥረን፡፡
አላሳፈሩሽም ወንዝሽን ተሻግረው
አንድ ነው ህልማቸው
አንድ ነው ቋንቋቸው
መሃላ ቃላቸው
ፍቅርን ይሰብካሉ
ተካፍሎ መብላትን
ላ‘ለም ያሳያሉ፡፡
እንዲህ እንዳሁኑ ዝናሽ በኛው ገኖ
ፍቅርሽ እንደ በሰቃ
ሰፍቶ
ኑሪልን በእጥፍ
ተባዝቶ፡፡
*
* *
21/04/98ዓም
No comments:
Post a Comment