እንዲህ ነው !
ስነ-ግጥም…የውበት ልቀት ነው
ስነ-ግጥም…….የሰው ልጅ አእምሮ ረቂቅ ውጤት ነው
ስነ-ግጥም …….የራሱ ፍጻሜ አላማ አለው
ስነ-ግጥም……….የስነ ጽሁፍ ፈርጥ ነው፡፡
© © ©
ለዚህ ነው በስነ-ግጥም የሰው ልጅ ስሜቱን የሚጭረው ነገር ሲያገኝ የሚያለቅስበት፤የሚስቅበት፤የሚከፋበት፤የሚዝነናበት፤ወዘተ………፡፡ እናም እንደቀልድ ከላይ የገጠምኳትን ግጥሜን ለረጅም ጊዜ ሳጥኔ ውስጥ ቆልፌ በቅርቡ ትንሳዬዋን አግኝታ ለአቅመ ንባብ ስትበቃ በርካታ ገጣሚያን ልብ ውስጥ ገብታ በራሳቸው እይታ የተሰማቸውን ለማለት የበቁት……….፡፡ መቼም ምን ያህል ልቤን አንደነካኝ ቃላት አይፈታውም ! ሁሉንም አመሰግናለሁ ፊት አውራሪ ገጣሚ ዮሃንስ ሞላ ትልቁን ቦታ ይይዛል ከዚህ በኋላም መሰል ግጥሞች ይቀጥላሉ…………እኛም እንጽፋለን !!!! ፡፡
© © ©
ቦንቡን
ቦንቡን ካልፈራኸው ንቀል ከእንብርቷይቆም ከመሰለህ ውበት መለከቷ
በሸንቃጣ ወገብ እንዲህ ተሞናድላ
በእንጆሪ ከንፈር በረዶውን ስላ
ደረቷ ሚሳኤል መያዙን ሳታውቀው
በአይኗ ወላፈን ፍቅርህን ሳትፈጀው
መሞትን ከመረጥክ
ትግደልህ ብያለሁ እሷም እንድትገልህ አንተም እንደመረጥክ …….
,
አርአያ መርቲ መተሃራ
አቤት ስልጣኔ
የጆሮ ተወዶ ዘንድሮ ጉድ ፈላ
ምንስ የቀረ አለ ያልተባሳ ገላ
ውበት ነው፣እብደት ነው ወይስ ስልጣኔ
ይህው ጉድ አሳየኝ ዝቅ ብሎ አይኔ
እምብርት ወግ ደርሶት ጉትቻ አጠለቀ
ተገንጦ በይፋ ይህው ፀሀይ ሞቀ
ቦዲ የተባለው መላ ቅጡ የጠፋ
ጡቶቿን አጋልጦ ያሳያል በይፋ
ሚኒ ደሞ ተብሎ ጣል የተደረገው
ሀፍረተ ስጋዋ ይህው አጋለጠው።
"እብደት ነው ውበት ነው ወይስ ስልጣኔ" ብዬ ቋጥሬ ካስቀመጥኳት ግጥሜ ከማስታወሻዬ ላይ የተወሰደች ነች።
የጆሮ ተወዶ ዘንድሮ ጉድ ፈላ
ምንስ የቀረ አለ ያልተባሳ ገላ
ውበት ነው፣እብደት ነው ወይስ ስልጣኔ
ይህው ጉድ አሳየኝ ዝቅ ብሎ አይኔ
እምብርት ወግ ደርሶት ጉትቻ አጠለቀ
ተገንጦ በይፋ ይህው ፀሀይ ሞቀ
ቦዲ የተባለው መላ ቅጡ የጠፋ
ጡቶቿን አጋልጦ ያሳያል በይፋ
ሚኒ ደሞ ተብሎ ጣል የተደረገው
ሀፍረተ ስጋዋ ይህው አጋለጠው።
"እብደት ነው ውበት ነው ወይስ ስልጣኔ" ብዬ ቋጥሬ ካስቀመጥኳት ግጥሜ ከማስታወሻዬ ላይ የተወሰደች ነች።