በዓሉ ግርማ
(1928 - 1976ዓ/ም)
ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢላባቡር ክፍለ ሀገር ሱዼ በሚባል ሥፍራ በ1928ዓ/ም ተወለዱ::
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርሥ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ት/ቤት: ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት አጠናቀዋል:: ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ እና ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ የቢ.ኤ. ዲግሪ ያገኙ ሲሆን: በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል::
ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶቻቸ ውስጥ "ከአድማስ ባሻገር" የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩሲያ ዊያን ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሺያሊስት ሕብረት ሪፑብሊክ ቀርቧል::
በጋዜጠኝነት
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤ የመነን መጽሔት፤ የአዲስ ሪፖርተር መጽሔትና;፤የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና: በኢትዮጵያ ራዲዮም አገልግለዋል::
የመጨረሻው መጽሐፋቸው "ኦሮማይ" በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግስት ሊደገፍ ባለመቻሉ: በ1976ዓ/ም ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን በቅቷል::
ድርሰቶቹ
* ከአድማስ ባሻገር
* የኅሊና ደወል
* የቀይ ኮከብ ጥሪ
* ሐዲስ
* ደራሲው
* ኦሮማይ

የዚህን
ድንቅ ጸሀፊ ልብ ወለዶች ከሞላ ጎደል አንብቤያቸዋለሁ ደራሲ በአሉ ግርማ ልብ የሚመስጥ ልብ ወለድ ጽፎልናል፡፡ እኔ ብዙ ማለት
አልችልም የተባለ ለመድገም ካልሆነ ! እጅግ በጣም የሚገርመኝ ግን ገጸ-ባህሪ አሳሳሉ ነው በተለይ
ሴት ገጸ ባህሪን ሲስል ያቺ ሴት በእውኑ አለም ያለች ያህል እንዲሰማን የማድረግ ሃይል አለው ምሳሌ ብጠቅስ…………. የአድማስ ባሻገሯ
ሉሊት ፤ኦሮማይ ላይ ያለቺውና የነገሰችው መቼም የማትረሳው ፊያሜታን ማንሳት እንችላለን በተለይ ፊያሜታ ጊላይ ምንጊዜም ከህሊናዩ
የምትጠፋ አይደለቺም !
በተለይ
በአሉ ግርማ በሷ ውስጥ የተናገረባት ፤ የልቡን የውስጡን የተነፈሰባት ደብዳቤዋን እጄ እስኪደማ በወረቀት ገልብጨዋለሁ…….. በተወሰነ
ጊዜዎች እስከ ዛሬ ድረስ እያነሳሁ አነበዋለሁ አይሰለቸኝም ! ምን ይሄ ብቻ ፊያሜታ ጊላይ የምተቀባው ቫኔል ፋይፍ ሽቶ ምን ጊዜም ከህሊና
አይረሳም ! ያን
ሽቶ አይቼው አሽትቼው ባለውቅም ጥሩ ሽቶ ባየሁ ባሸተትኩ ቁጥር ተመስጫለሁ፤አስቤዋለሁ፡፡ መጽሀፉ በወጣ ሰሞን የሃገሬ ቆነጃጅት
ወጣት ሴት ሁሉ በተለይ በመዲናችን አዲስ አበባ ፊያሜታ ምትጠጣውን መሎቲ ቢራ በስፕራይት መጠጣት ፋሺን ሆኖ ፤ሀገሩን አጥለቅልቆት
እንደነበር በወቅቱ የነበሩ ሰዎች አጫውተውኛል ፡፡ የዚህን ያህል ደራሲው ገጸ-ባህሪ መሳል ይችልበታል ! ሌሎች
ብዙ ልትሉ ትችላላሁ ወይ ብትሉን ደስታዩ ወደር የለውም፡፡ እኔ ግን ፊያሜታን በደራሲው ልብ ውስጥ ሆኘ እያሰብኩ የገጠምኳትን ግጥም
በቀጣይ ጊዜ እለጥፈዋለሁ፤ አስነብባችኋለሁ እስከዛው በደራሲው የመጨረሻ ቃል እንሰናበት፡፡
#............;
እንባ
እንባ ይለኛል
ይተናነቀኛል………
እንባ
ግን የታባቱ
ደርቋል
ከረጢቱ
ሳቅ
ሳቅም ይለኛል
ስቆ
ላይስቅ ጥርሴ
ስቃ
እየነደደች
መከረኛ
ነፍሴ፡፡
© © ©
ኦሮማይ
No comments:
Post a Comment