Friday, April 27, 2012

ናፍቆቴን ነጠኩኝ


ናፍቆቴን ነጠኩኝ
    አንድ በኤለክትሮኒክስ መረጃ መረብ የተዋወኩት ወዳጄ እንደዋዛ በስራ አጋጣሚ በአንድ በኩል እንጀራ§ን እየጋገርኩ በአንድ በኩል የመጻፍ ማወቅ ስሜቴን እየተወጣሁ ሳለ ተዋወቅን ፡፡  ገጣሚ ነው ደስ ደስ የሚል ግጥሞች ይጽፋል….. እናም እኔ እንደቀልድ የምለጥፋቸውን ግጥሞች በጣም ይወዳቸዋል ሳይታክት አስተያየት ይሰጠኛል………..! በጣም ሳላመሰግነው አላልፍም ምክንያቱስ ብትሉ ስንት ዓመት ከወረቀት ከማንበብ ተለይቼ እኮ ነው ደንገት መነቃቃት የጀመርኩት ……..ሀሪፍ አይደል !!!! አንድ ግን አክሎ አስተያየት ሠጠኝ ፡፡ ምን አለ መሰላቹ…..
# ወዳጄ አደም ግጥሞችህን በጣም ወዳቸዋለሁ ተመቹኝ ግን ማብራሪያ ታበዛለህ ; አለኝ ፡፡
   ልክ ነው ከምለጥፋቸው ግጥሞች ጋር የተለያዩ ታሪኮች አሉ ግን የግጥሙ ማብራሪያዎች አይደሉም እራሳቸውን የቻሉ (የጉዞ ማስታወሻ ፤ወግ፤ገጠመኝ፤ወዘተ…… ) ሊሆን ይችላል ወይም ናቸው፡፡ ከሙሉ ትረካ ቦጨቅ እያደረኩ ነው የምለጥፈው እንጂ ሙሉ ሙሉ ታሪኮች ናቸው ፡፡ የጻፍኩትን ሁሉ ቢሆንማ  አታነበውም ብዙ ነዋ ! እሳት ላይ ሆኖ እንዴት ይነበባል ???? መስመር ላይ ደግሞ ሰዎች ይጠብቁሃል ምናልባት በፌስ ቡክ የለጠፈችውን ፎቶ አይተህ የጠስካት ወይም የተዋወካት ልጅ ልታወራህ ትፈልጋለች ስለምትወደው ፒሳ፤ ስለምትጠላው  ነገር ወይም ሻኪራ ስለለበሰቺው ልብስ እያወራችህ ነው….. መቼም ቀይ ሲበራ ደብዳቤ (message) ሲደርሰው ማን ደስ የማይለው አለ ? ሌላው ደግሞ በእርግጥ የእውነት ብዙ ጊዜ ስትፈልጋት የኖረች የድሮ የሰፈር ልጅ አግኝተህ ናፍቆትህን እየተወጣህ ሊሆን ይችላል ፎቶግራፏን ስታይ በጣም ወፍራብህ፤ወይም አምሮባት ወይም ባል አግብታ ከልጆችዋ ጋር አንዴ ዛፍ ስር አንዴ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ የተነሳችውን ምስሏን እያደነቅህ ይሆናል….. ስለ ተለዋወጥካቸው ፖስት ካርዶች፤ስለ ድሮ ትምህርት ቤት፤ስለፍቅር ደብዳቤ……. ሰፈር ውስጥ በአንዲት ሴት ልጅ ስለተጣሉት ጎረምሶች እያወራህ ነው……. ስለዚህ የተቦጨቀ ታርኮች መለጠፍ የግድ ሆነ……
                  "   "   "
መቼ ለት ነው….; ቅዳሜን ወዳታለሁ ብያችሁ ነበር አይደል …..! አዎ በጣም ነው የምወዳት ከምወዳቸው ወዳጆቼ ጋር የምታገናኘኝ ቀን ነች ሁላቸውም የተለያየ ስራ፤ ፍላጎት ፤ዝንባሌና ባህሪ የተላበሱ ናቸው በተለይ ከቀጥር በኋላ ደስ ሚል ጊዜ እናሳልፋለን እዛም እዚም ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር ይከፈታል ወግ ይጠረቃል ፤ፖለቲካ ይታሻል ፤ይወቀጣል፤ ትንታኔ ይሰጥበታል፤ ዓለም እንዴት ሰነበተች እንላለን ማነው ቴሌቪዥን መስኮት ላይ ብቻ ለሚቀርቡት  ጋዜጠኞች የፈቀደው ???

   እና እኛም ስለ ቢዮንሴ የልጅ መውለድ፤መብላትና መጠጣት  ከሚያስጨንቀው ሰው አንስቶ እስከ  የሃገራችን ፖለቲካ ነጻ  አስተያየት  ስለ ኢኮኖሚያችን ማደግ ፤መመንደግ  የግል አስተያየት ይሰጣል ወይ ብንሰጥስ፤ ደግሞ በመሃል ለማጣፈጫ ስለ ቆንጆ ሴት ልጅ ውበት ቁንጅና…... ትላንት ስለጠበስካት ወይም ስለጠበሰችህ ልጅ ስለ እንትና ገርል ፍሬንድ የምትለብሰው ልብስ የቀን ውሎ የሳምንት ከርሞ ይነሳል ይጣላል ደስ ይላል….! ፡፡
እንደወትሮው ሁሉ ሁሉም ወዳጆቼ ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል አንድ ጓደኛችን ግን ከቦታው አልተገኘም……. አዎ ትዝ አለኝ ለአጭር ጊዜ ኮርስ ወደ ህንድ ሃገር ሄዷል በጣም የሚያጫውተን play maker ስለሆነ የዛሬውን ውሎ ቀዝቀዝ አድርጎታል……ሙዚቃ አለ የአስቴር አወቀ የድሮ ካሴት አየሩን ተቆጣጥሮታል
            # ምነው እግር አዋጣህ እንዴት ፈረደብኝ ;
            # ያም አንተን ያም አንተን አዩብኝ መሰለኝ ;፡፡
ድንገት # ሃይ እንዴት ናችሁ? ; የሚል ህንድ የሄደውን የጓደኛችንን ድምጽ ከአንዱ ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር ውስጥ ተሰማ አላመንኩም እውነት ከምሬ ነው! ይባስ ብለው ጠሩኝ የናፈቀኝ ወዳጄ ፊት ለፊት ተፋጠጥን………እናም ብዕሬን ከወረቀት ጨበትኩ ፡፡
ከዛል ጊዜ ጀምሮ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ሰካይፒ የሚባለውን የመረጃ መረብ ተጠቅሜ አይቼ እንደማላውቅ ልንገራችሁ ! የነገን አላውቅም፡፡
                 "    "    "

5 comments:

  1. ሙዚቃ አለ የአስቴር አወቀ የድሮ ካሴት አየሩን ተቆጣጥሮታል
    # ምነው እግር አዋጣህ እንዴት ፈረደብኝ ;
    # ያም አንተን ያም አንተን አዩብኝ መሰለኝ ;፡፡
    በእርግጠኝነት አስቴር ይኸን ዘፈን አሁን እንዴህ ብላ ታንጎራጉረው ነበር
    ምነው ጊዜ አጥህ ለእኔ እንዴት ፈረደብኝ
    ከዚህ ኢንተርኔት ላይ ደሞ ማንን አየኸብኝ…….ምናምን
    ሰላም ይረፉ

    ReplyDelete
  2. The poem is excellent, but, the commentary (that I liked too) came out partly gibbrish.

    ReplyDelete