ሀዋሳ ቤሌማ……!
1

•••
ዛሬ የምናወራላት ሀዋሳ የዛሬ መጠርያዋን ከማግኘቷ ሀምሳ
ዓመት በፊት “አዳሬ” የሚባል ስፍራ ነበር ትርጓሜውም “የግጦሽ መሬት” ማለት ነው እናም ከተማዋ የከተማ ወግ ስታገኝ ሀዋሳ ተብላ
መጠራት ጀመረች ፡፡ ስሙ የተገኘው ከሃይቁ በመኮረጅ ሲሆን ቃሉም ሲዳምኛ ሲሆን “ሰፊ” ወይም “የተንጣለለ” እንደማለት ይሆናል
፡፡ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጡ እና ከባቢያዊ ሁኔታውን ስንመለከት የዛሬው የሲዳማ ዞን ወይም በቀድሞው የሲዳማ አውራጃ በስተሰሜን የሚገኝ ቦታ ሲሆን ከሻሸመኔ ከተማ
አስተደቡብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች ፡፡ከሀዋሳ በስተምእራብ የሀዋሳ ሃይቅ ተንጣሎ ሲገኝ በስተምስራቅ
ደግሞ የወንዶ ገነት ተራራ አዘቅዝቆ ይመለከታታል ፡፡ ቦታው የስምጥ ሸለቆ አካል ሲሆን ልዩ ከሚያደርጉት መገለጫዎች ዋነኛው በዓመት
ሁለት ጊዜ የዝናብ ወቅቶች ያለውና ለም መሬት በደን የተሸፈነ አካባቢ መሆኑ ነው፡፡
ይህ የዛሬዋን ሀዋሳ ነባራዊ ሁኔታ የለወጠው ታሪካዊ ክስተት
የተፈጠረው በ1949 ዓም ነው ፡፡ ጉዳዩም የተከሰተው አጼ ሃይለስላሴ በ1949 ዓም በያኔው አጠራር የሲዳሞን ጠቅላይ ግዛት ለመጎብኘት
በሚጓዙበት ወቅት የሃዋሳን አካባቢ ሲያቋርጡ በተመለከቱት የቦታው አቀማመጥና ተፈጥሮአዊ ጸጋ ተማረኩ፡፡ በወቅቱም የጠቅላይ ግዛቱ
ገዢ ለነበሩት ለደጃዝማጅ (በኋላ ራስ) መንገሻ ስዩም ትእዛዝ አስተላለፉ……“
በዚህ ቦታ ዘመናዊ እርሻ ልማት እንዲከናወን አዲስ ከተማም እንዲሰራ እንዲሁም በሃይቁ ዳር ቤተመንግስት እንዲሰራ…..” የሚል ትእዛዝ
ነበር፡፡ በመሆኑም ራስ መንገሻ ስዩም ያስተዳድሩት ከነበረው የአርሲ ጠቅላይ ግዛት ተዛውረው የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛትን እንዲያስተዳድሩ
ህዝቡንም እንዲያገለግሉ ሹመት አገኙ፡፡ ያኔ የጠቅላይ ግዛቱ ዋና ከተማ ይርጋለም ነበር ፡፡ ( በዚህ አጋጣሚ ከሃዋሳ ከተማ
43 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቆ የሚገኘው ይርጋለም ከተማ ብዙ ያልተዘመረለት የገጣሚና የውስጥ ቀዶ ሃኪም አብረሃም ፈለቀ (ቢላዋና
ብዕር) የምትል የግጥም መድብል አለው)፤የነ ገጣሚ ደራሲ አብረሃም ረታ ፤የነ ገጣሚና ጸሃፊ ተውኔት ደበበ ሰይፉ የትውልድ ከተማ ነው፡፡ ሄጄ የማየት እድሉ አጋጥሞኛል….!
በተለይ ኪነ ጥበብን በሚያደንቅና በዙርያው ላይ ላለ ሰው በሚያደንቃቸው
የደራሲዎች ሃገር ሲገኙ ምን ያህል ደስታ እንደሚሰማው እኔ ምስክር መሆን እችላለሁ፡፡ እንደ አጋጣሚ ሁሉም በህይወት የሉም…… ምናልባት
ወደፊት በተለይ ብዙ ስላልተዘመረለት ሁለገቡ ባለሙያ ስለ ዶክተር አብረሃም ፈለቀ ካየሁት ከሰማሁት ካነበብኩት ለማካፈል ለመጨዋወት
እንሞክራለን) ፡፡
ራስ መንገሻ ይርጋለምን በሚያስተዳድሩበት ወቅት ከተማዋ
ወደፊት ህዝቡ ሲጨምርና የማህበራዊ እኮኖሚያዊ ተቋማት ሲስፋፉ አብሮ
መስፋፋት ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ካጠኑ እና ካስጠኑ በኋላ ለውሳኔ በማቅረብ በ1960 ዓም የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማነት
ከይርጋለም ወደ ሀዋሳ መዛወሩ እውን ሆነ…..፡፡ ይህ አጋጣሚ ለሀዋሳ እድገት ትልቅ እድል የፈጠረ ሲሆን ለይርጋለም ከተማ እድገት
መጎተት መንስኤ ሊሆኑ ከሚችሉ ምክንያቶች እንደዋንኛው የሚቆጠር ይመስላል፡፡ በዚህም የተነሳ የሀዋሳ ከተማ ታሪክ ወደሌላ ምእራፍ
ተሸጋገረ ፡፡
2

ከግቤ ባሻገር አለች እረ አንዲት ሰው
በፍቅር በናፍቆት ልቤን የምትወዘውዘው
አቦል ጀባ ብላ ቡናዋን ብቀምሰው
ልቤ ወደ ጂማ ሱስ አመላለሰው
ቤትሽ ጅማ ነው ወይ…….
ጅማ እንውረድ……… እያለ የአባ ጅፋርን ሃገር እያወደሰ
የሚያቀነቅነውን ዘመን ተሸጋሪ የማይሰለች ዜማና ግጥም የደረሰው ከሃያ አንድ ዓመት በፊት ለኪነጥበብ ሙዚቃ ስራ በሄደበት አጋጣሚ
በጉዞ ወቀት የጊቤ በረሃን አቋርጦ ጅማ ደርሶ ባለው ባየው ነገር ተገርሞ ተደምሞ…! ከዛም አልፎ ጅማ ድረስ ትርኢቱን ሊያሳዩ የሄዱትን
የስራ ባልደረቦች ጨምሮ አንድ ታዋቂ የጅማ ሰው ቤት የእንኳን በደህና መጣችሁ የቡና ስነስርዓት በሚደረግበት ወቅት ቡናውን የምታፈላው
የጅማ ቆንጆ ልጅ ውቧቷ ትህትናዋ ፤መስተንግዶዋ ስቦት እሷን ዋና ገጸ ባህሪ አድርጎ ጅማና አካባቢዋን የገለጸበትን ድርሰት እዛው
ጽፎ እንደመጣ አጫውቶኛል፡፡ለዚህም ይመስለኛል በተለይ ተፈጥሮ….! ሃገርን እያወደሰ በስሜት እያነሳ የጻፋቸው የሙዚቃ ግጥም ድርሰቶቹ ቀላልና የማይሰለቹ የሆኑት ወይም
እውነት እውነት የሚሸቱት እቦታው ከስሜት ሆኖ ስለሚጽፋቸው ይመስለኛል፡፡
ነውም ደግሞ…….እስቲ ልብ ብላችሁ አድምጧቸው፡፡
የነገር ዳርረዳርታዬ ወዲህ ነው ሃዋሳ ለዚህም ትመቻለች
እውነት ትመቻለች….የነገ ሰው ይበለንና አጋጣሚዎችን እናነሳለን……..