Thursday, May 10, 2012

እሳት ወይ አበባ


እሳት ወይ አበባ

 ሌት ከዋክብቱ  እንደ ፀደይ
አጥለቅልቆን  በቀይ አደይ
ሰማዩ  ሥጋጃ  አጥልቆ
ተሽለምልሞ  አንጸባርቆ
ፈክቶ አሸብርቆ  ደምቆ
በአዝመራ  በአጥቢያ  ዐፀድ  ሰፍኖ
የዓደይ  አዝርዕት  ተከሽኖ
በዕንቁጣጣሽ  ሰብል  ታጥኖ
ኢዮሃ  አበባዬ  ሆኖ፥
ጨረቃዋ  ከቆባዋ፥  ከሽልምልሚት  እምቡጧ
ብላ ከሰንኮፈንዋ፥ ተንዠርግጎ የእንኮይ ቡጧ፥
ድንግል  ጽጌ-ረዳ  ፈልቃ
ፍልቅልቂት  ድምቡል ቦቃ
ተንሠራፍታ  የአበባ  ጮርቃ፥
ታድያን  ብሌኑ  የጠጠረ
ባሕረ-ሃሳቡ የከረረ
የውበት ዓይኑ የታወረ
ልበ-ሕሊናው  የሰለለ
አይ፥ አበባ አይደለም አለ፤
አይ፥ እሳት አይደለም አለ፤
ያልታደለ።
ሰማይ  ጨለማ  ነው እንጂ፥  እሳት አደል ብሎ ካደ
እቶን  ባይኑ  እየነደደ።
ከዋክብቱ  እንደ  ችቦ
በነበልባል  ወርቀ  ዘቦ
ከፅንፍ  ፅንፍ  አውለብልቦ
ደመራው  እየተመመ
እየፋመ  እየጋመ
ደመና  እንደንዳድ  ሲነድ
መንጸባርቅ  ሰደድ  ሲወርድ፥
በራሪ  ኮከብ  ተኩሶ
በአድማሳት  እሳት  ለኩሶ
ይኸ እንደኔና  እንዳንቺው፥  የውበት ዓይኑ  የሰለለ
ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ፥  እሳት እኮ አይደለም አለ፥
ያልታደለ።

ይቅር ብቻ  አንናገርም፥
እኔና  አንቺ  አንወያይም፤
ለውይይት  አልታደልንም
እንዲያው ዝም፥ እንዲያው ዝምዝም።
አበባ አንሆን ወይ እሳት
ተጠምደን  በምኞት  ቅጣት
ሰመመን  ባጫረው  መዓት
ዕድሜ አችንን እንዳማጥናት፤

እሳት አንሆን ወይ አበባ
በሕቅ  እንቅ  ስንባባ
ባከነች  ልጅነታችን፥ እየቃተትን ስናነባ
ሳንፈጠር  በሞትንባት
ሳናብብ  በረገፍንባት
ሳንጠና ባረጀንባት
አበባ ወይንም እሳት፥  መሆኑን ብቻ አጣንባት።
© © ©

ከጸጋዬ ገብረ መድኅን

Monday, May 7, 2012

ኮከቤን ፍለጋ


         ፍቅር ከራስ ወደድነት የነጻ ነው! ፍቅር ድንበር ዘለል ሀይማኖት አያውቅም !ፍቅር ጠረን ነው፤መላመድ ነው ! ፡፡ ይሄ አባባል አዲስ ላይሆን ይችላል ፡፡
        ትላንት አንድ እጅግ በጣም ደስ የሚል የጋብቻ ስነ ስርአት ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሙሽሪት ዘመድ ናት የአጎቴ ልጅ…….እጅግ ውብ ናት ለምን የሞዴል ስራ እንደማትሰራአይገባኝም ወይም መንገዱን አላገኘቺም…..ማለቴ ተክለ አቋሟ የዛን መሰረት ያሟላ ይመስለኛል……ዛሬ ላይ የእርሻ ሰራተኛ ሆና አፈር ትቆፍራለች፡፡
    ሰርጉ እየተካሄደ ነው ብዙ እድምተኛ ተገኝቷል ገምት ብትሉኝ ከ200 ነላይ ይሆናሉ ወደ 15 የሚሆኑት የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው ምክንያት ሙሽራው የውጭ ሃገር ዜጋ በመሆኑ
# ትወዳታለህ ወይ ? ;
አልኩት የሞኝ በሚመስል ጥያቄ
# በጣም እንጂ በጣም ;
ቃላቶች እያጠሩት መለሰልኝ
# ያገባኋት እኮ ብወዳት ነው ; አለኝ አከለና
# ማለቴ ሃይማኖት ባህል ችግር አይፈጥርም ? ;
# ይገርምሃል ይሄን አስቤው አላውቅም ; አለኝና እሩቅ ተጓዘ በሃሳብ….. ጨመረናም
# በቃ በጣም እወዳታለሁ የህይወቴ አጋር እንድትሆነኝ ፈቅጃለሁ ;
        ወደ ድግሱ ፊቱን መለሰ …..ሁለታችንም በኛ ባልሆነ ቋንቋ በተሰባበረ እንግሊዘኛ ነበር የምናወራው እሱ ጀርመን እኔ ሃበሻ…… ፡፡ በድግሱ መጨረሻ ላይ ከታዳሚዎች ፤ከጓደኛ ፤ከመስሪያ ቤት ባልደረቦች፤ የስጦታ የመልካም መግለጫ ጋርድ እየተበረከተ ነው፡፡ ድንገት ባነንኩ ለካ ስጦታ መስጠት ነበረብኝ በጣም ተሰማኝ ፡፡ እንደቀል ግን በሞባይ ፎቶ አነሳቸው ነበር ከዛም አልፎ ከሙሽራው ጋር በነበረን ቆይታ አንድ ነገር ልቤ ውስጥ ቀረ ……እናም ሙሽራውን እያሰብኩ ይህች ግጥም ጻፍኩ ወይም ተወለደች እናም ስጦታ ትሆነኝ ዘንድ ሰጠኋቸው፡፡   

Friday, May 4, 2012

ነፍሴ ገዳም ግቢ


          የደራሲና ጋዜጠኛ በአሉ ግርማን የህይወት ታሪክ ስናወጋ የመጨረሻ መጽሃፉ በሆነው በ #ኦሮማይ; ዙርያ በስሜት ተጨዋውተን እንደነበር ላስታውስ…….፡፡ አዎ በተለይ ደራሲው ይህን የመጨረሻ የሆነውን ልብ-ወለድ መጽሃፍ ሲጽፍ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችልና በመጽሃፉ ደስተኛ ያልሆኑ በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ባለስልጣኖች እንደነበሩ ጠርጥሯል……ወይም ያውቅ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ የስራና የእውቀት ጓደኞቹ በተለያየ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስነብበውናል፡፡ ይህንን ህይወቱን ዋጋ ያስከፈለውን መጽሃፉን ከመጻፉ በፊት በተለያዩ ጊዜ በሚሰጣቸው መግለጫዎች ወይም በሚያገኛቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ጽኑ እምነቱን፤አንድ ደራሲና ጋዜጠኛ ምን ማድረግ እንዳለበትና የሚጠበቅበትን እንዲህ ሲል መናገሩን ማንበቤን አስታውሳለሁ……፡፡ # ድፍረት የሌላት ብዕር ወረቀት ባታበላሽ ይመረጣል…..! ከአድር ባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ብዙ ያናገራል ! ; ይለናል…..፡፡
    ይህ እንግዲህ የደራሲውን ድፍረትና ለቆመለት አላማ ታማኝ መሆኑን……! እንጽፋለን ለምንልና ለምናስብ……. እውነተኛ ብዕር ምንጊዜም ከመቃብር በላይ ሊያስቀምጥ እንደሚችል አስተምሮን አልፏል፡፡ በዚህ መሃል ፊያሜታ አለች…..፡፡ መቼም በኦሮማይ መጽሃፍ ውስጥ ስሜቱን የሚተነፍስባትና መሪ ገጸ ባህሪው ስለሆነችው ፊያሜታ አውርቼ እንደማልጠግብ እያሳበቀብኝ መሆኑ ይገባኛል……!፡፡ በኔ ብቻ የሚቆም ግን አልመሰለኝም፡፡ አንድ ወቅት የጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዩ ገ/አብ # የጋዜጠኛው ማስታወሻ ; ሳነብ እንዲህ የሚል አነበብኩ፡፡
                          ©  ©  ©
      # # ኦሮማይ ; ን መጽሃፍ መርቄ ከከፈትኩ በኋላ በግብዣው ስነ ስርዓት ወቅት በመጪው የስነ-ጽሁፍ ህይወቴ ላይ አብይ ሚና የተጫወተው ገጣሚና ደራሲ አበራ ለማ ጋርም ለመተዋወቅ በቅቻለሁ፡፡ በዘመነ ደርግ አበራ ለማ የኦሮማይ ገጸ-ባህሪ ለሆነቺው ፊያሜታ የቋጠራትን #ፊያሜታ እምባባ; የተሰኘቺው ግጥምም ከኦሮማይ መጽሃፍ ጋር በዚያኑ እለት ነጻ የወጣች ሲሆን በወረሃ መስከረም 1984 ዓም ግጥሟ የዛሬይቱ ጋዜጣ ላይ ታትማለች ፡፡ ጥቂት ስንኞች ልቀንጭብላቹ ; ይለናን፡፡
እነሆ እናንተም ግጥሟን ተቋደሱልኝ….
ፊያሜታ፡- የጋዜጠኛ ማስታወሻ
         የጋዜጠኛ መተንፈሻ
ልብሽ በነ ሰውየው ሴራ ሲንገላታ
ፍቅር መች ሆኖ ፊያሜታ
የልብ አፍቃሪ ካገኘው ላይረታ
ፊያሜታ፡- ሰው እንጂ ፍቅር ምን ገዶት
እውር መባሉ በቀተረው ተሲያት
ባምባሽ በቀበሌሽ ልብ ታወረ
ብርሃን ፈልጎ ጀንበርን ጫረ
አንቺ ጽብቅቲ የሰሜን ዋልታ ጮራ
የታሪኩ እምብርት መቋጠርያ የበአሉ ደመራ!፡፡
         ©   ©   ©
ገጽ 120-121

Wednesday, May 2, 2012

ልዑል ዓለማየሁ


                              ልዑል ዓለማየሁ

        ዓፄ ቴዎድሮስ ደራስጌ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠው ሳለ አንድ ወታደራቸው ወደ ርሳቸው ቀረበና "ጌታዬ አንዲት ሴት አገኘሁ ፊትዋም እንደ ፀሐይ የሚያበራ ነው" አላቸው:: ልጅቱም በኃላ ወደ ቤተ መንግስት ቀረበች: ስምዋም ጥሩነሽ ውቤ የደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ልጅ ነበረች::
ንጉሱም አይተዋት "እውነትም ወርቅ ናት" በማለት አገብዋት::
በዚህ ወቅት ንጉሠ ነገሥቱ አባትዋን ራስ ውቤን አስረዋቸው ነበር:: ራስ ውቤ የሰሜን ወልቃይት; ፀገዴ; ትግራይ; ሰራየ; ሐማሴንና; አንጎት(ሰሜን ወሎ) አስተዳዳሪ ሲሆኑ:: ከአፄ ፋሲለ ደስ የሚወለዱ ስለነበሩ: ለንጉሥነት የሚገዳደሩ ነበሩ::
የጥሩወርቅ(ጥሩነሽ) እናት ደግሞ ወይዘሮ ላቂያየ የተባሉ: የትግራይ መሣፍንት ዘር ነበሩ::
ከኒህ ሚስታቸው ደጃዝማች ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የተባለውን: ከሁሉ በላይ የሚወዱትን እርሳቸውን እንዲተካ ያጩትን ልጅ ወለዱ::

ልዑል ዓለማየሁ 1853/ ተወልደው: በምርኮ በተወሰዱበት እንግሊዝ አገር ሊድስ ዩርክሻየር 1870/ ሃገሬ ናፈቀችኝ እንዳሉ 17ዓመት ዕድሜያችው በሣንባ ምች ታመው ዓረፉ::

ከመንታሞች መንገድ