Thursday, October 11, 2012

ቅጽበቴ




አደም በዚህ መልክ እንደገና ፃፍኩት ያለቀ ስላልመስለኝ ከይቅርታ ጋር 
ቅጽበቴ
“…ጋልቤ ባልጌ ዱብ ስል ከራሴ ከስሜት ፈረስ
ከሄድኩበት ዓለም በድንገት ስነቃ
ያቺ በለሊቱ አብራን የነበረች ጠፍታብኝ ደማቋ ጨረቃ 
ውስጤ ተረብሾ ጭለማ ሲከበኝ መሃላዬ ፈርሶ ሲገለጥ አመሌ
ቅጽበት ቃሌን ክቦ ቅጽበት ቃሌን ሲያፈርስ
ግልገሌን ሳጠልቅ ታየው ስትራመስ 
ማን ይሆን ኃላፊው ቅጥ ላጣ ስሜቴ
በቅጽፈት እይታ አልጋ ላይ ለሚወድቅ መጥፎ ማንነቴ፡፡”
ØØØ

ትህትና ገ/ጻድቅ

አቦል ጀባ







አቦል ጀባ
የቡናማ ሽር ጉዱ
ይጀምራል ከምጣዱ
ቆላ ቆላ ጣጣ ጣጣ
በጭስ ሙላት በጎፈጣ
ከጀንፈሉ በሚወጣ
የመአዛ ረብጣ
ቤትን ሞልቶ
ከሩቅ ሸትቶ
ደሞ ከመውቀጫው ድም ድም
እስከሚደቅ እስከሚልም
ሁልም በዬ በቱ መታ መታ
የቀትር እሩምታ
በጀበና ተሰልቅጦ
ከእሳት ላይ ተቀምጦ
እስኪሰክን እስኪፈላ
ጎረቤት ጠርቶ ፈላ
እማዬ ስትላችሁ
ቡን እንጠጣ እባካችሁ
ከዚያማ ወዳጅ ሁሉ ተሰባስቦ
ቄጠማ ተጎዝጉዞ ተደርድሮ ስኒው ቀርቦ
ቁርስ ተቆርሶ
በጨዋታ ማር ተለውሶ
እጣን ተጭሶ ተንቧልቆ
ቁም ነገር ተነግሮ በቀልድ ተስቆ
ይበላል ይጠጣል ይመረቃል
ባህላችን ይናፍቃል
በያላችሁበት አቦል ጀባ
አይክፋችሁ ሆድ አይባባ:)
YYY
ሰኢድ

Wednesday, October 10, 2012

ይናፍቀኝ ነበር







እንደተለመደው ቀድሞ የምንሰማው
ደግ ደጉን ብቻ ''ናፈቀኝ'' ሲባል ነው
ለካ የሚናፍቀው ደግ ብቻ አይደለም
ገጣሚው እንዳለው ይናፍቃል ክፉም
በዚህ አጋጣሚ ታወሰኝ ዘፈን
ለናፈቃት ፍቅሩ እንደዚህ ያላትን
''....
የሳቅ ብቻ አይደለም እቴ ያንቺ ትዝታ
ኩርፊያሽ ይናፍቃል የተለዩሽ ለታ...''
            ØØØ
       ብሌን ከበደ

መጽሐፍ የሚያነብ ትውልድ እንፍጠር !!!


ትንሳኤው ናፈቀኝ


በርካታ የአለማችን ህዝቦች እንደመብላትና መጠጣት ከዛም በላይ የመናገር የመጻፍ እና ሃሳብ የመስጠት መብታቸው ተገፎ በመሸማመቅ ባለመኖር መኖር የእንጥልጥል ህይወት የሚመሩ ቤት ይቁጠራቸው…..! ፡፡ብዙ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ሰፋ አድርጌ አስባለሁ ፤ሳላውቀው እጨነቃለሁ፤ ለምን ግን እላለሁ…..! ይሄ የአንድ ጤነኛ ሰው አስተሳሰብ ነው ብዩ ባስብም ከዛ በላይ ምን አደርጋለሁ ? ይህ ጉዳይ ስሜቴን ሲነካኝ በግጥም አስፍሬ አስቀመጥኳት፡፡ እስቲ እዮብ፤ዘላለም ጥላሁን፤ዮናስ እንዲሁም ሌሎች ወዳጆቼ በቀና መንፈስ ተወያዩ….. መልካም ንባብ፡፡

ስራ ክቡር ነው..!!


ይድነቃቸው በቃ…!!!