Thursday, October 11, 2012

አቦል ጀባ







አቦል ጀባ
የቡናማ ሽር ጉዱ
ይጀምራል ከምጣዱ
ቆላ ቆላ ጣጣ ጣጣ
በጭስ ሙላት በጎፈጣ
ከጀንፈሉ በሚወጣ
የመአዛ ረብጣ
ቤትን ሞልቶ
ከሩቅ ሸትቶ
ደሞ ከመውቀጫው ድም ድም
እስከሚደቅ እስከሚልም
ሁልም በዬ በቱ መታ መታ
የቀትር እሩምታ
በጀበና ተሰልቅጦ
ከእሳት ላይ ተቀምጦ
እስኪሰክን እስኪፈላ
ጎረቤት ጠርቶ ፈላ
እማዬ ስትላችሁ
ቡን እንጠጣ እባካችሁ
ከዚያማ ወዳጅ ሁሉ ተሰባስቦ
ቄጠማ ተጎዝጉዞ ተደርድሮ ስኒው ቀርቦ
ቁርስ ተቆርሶ
በጨዋታ ማር ተለውሶ
እጣን ተጭሶ ተንቧልቆ
ቁም ነገር ተነግሮ በቀልድ ተስቆ
ይበላል ይጠጣል ይመረቃል
ባህላችን ይናፍቃል
በያላችሁበት አቦል ጀባ
አይክፋችሁ ሆድ አይባባ:)
YYY
ሰኢድ

No comments:

Post a Comment