Wednesday, June 6, 2012

እንባዋ


እንባዋ ቁ2
'ንባ እያማጉ
ከንፈር ከተበላ
ታድያ እንዴት
ሊሆን ነው
ከከንፈር ሚፈሰው
የማሩስ ወለላ....?፡፡
ሞንጫሪት
©©©
Mesert le

እንባዋ ቁ3
እናትክን ተመልከት…..
ሰርታ ጥራ ግራ
ሁሉን ልታስደስት
በገበታው ማጀት…..
        ወጡን ስትወጠውጥ
ሽሮ ስጋ አይደል…..
        ወጡን የሚያጣፍጥ
ስላወቁ ሴቶች……….ጨው ጠብ ካላለ
           ጥፍጥና ሽሮ እንደሌለ
ይህን ስላወቁ አይናችን……..
                እንዳይዞር ገመዱ ማሰሪያው
ወጥን በጨው ከንፈርን በንባ ' ነው  
      ወዳጄ ወንድ ሚታሰረው::
ያኔ ነው ጥፍጥናው
 አልያ አኞ ነው ታኝኮ ማይጥመው
እና    …..
እወቀው  የጅምርህ  ኑሮ
የፍቅርህ  እምነት  ነው
የሷነቷ  ፈትልህ  ነው
የዘመናት  ቱባ ::
© © ©
Arhay merti mekash

የፊደል ጨዋታ


የፊደል ጨዋታ ቁ 2
ካቡጊዳ ሰፈር ከኛው ከወንዛችን
የቀዳኀው ወይኑ ይጥም ለጆሮአችን
         ብለህ የተየብከው
የግጥም ገነት በር መክፈቻው ቁልፉ ነው….

….
ግና በኔ ሀሳብ ሚስቴ እንዳወቀች
….
ሞራልና ድጋፍ ሰቷል ከተባለች
ብላ ብላ
ከፊደል ተራ ወጥታ
......  ያረገችኝ  ለታ
መድረሻም  የለኝም  ከፊደል  ገበታ …..አቦ  ምርጥ ነው!!!
© © ©
አርአያ መርቲ መካሻ

የፊደል ጨዋታ ቁ 3

      
ምንም ባቷ ቢመስል በቅቤ የታሸ
አትራፊው  እሱ ነው  እንዳላየ  የሸሸ
        
መከራው  ብዙ ነው ሲወጡ  ተነክሮ
በኋላም ያመጣል  ፀፀትና  ሮሮ
            
ማን  ጥሩ  አተረፈ  ከከበር ቻቻ
ምነው በቀረብኝ  ኖሮ  ማለት ብቻ
           
ምን  ሲጨፍር  ቢያድር  መስሎት  ያለው  ደስታ
ብዙ  ነገር  ቢያደርግ  በመጠጥ  ሞቅታ
ትጠብቀዋለች  ፀፀት  በሩዋን  ከፍታ
ደሞ በተራዋ  ደስታ  በሯን  ዘግታ
ይሄ  ነው  ምላሼ  ለፊደል  ጨዋታ፡፡
© © ©
Mulex peace
ሁለታችሁንም ገጣሚያን አመሰግናለሁ እንዲህ ነው ስሜት በግጥም ሲገለጽ!!! ለዚህም ነው……………………….
        ስነ- ግጥም የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ብዙ የህይወት ጉዳዮችን የሚያነሳ የስነ ጽሁፍ ዘርፍ ነው፡፡እንዲሁም የሰው ልጅ ሰው ከሆነበት ቋንቋውን ኪነ -ጥበብ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ አኳያ ሲታይ መጀመርያ በድርሰት መልክ የተከሰተ የቋንቋ ጥበብ ነው፡፡
     እያናዳንዱ ግጥም ጣዕም አለው፡፡ ጣዕሙ የሚለየው ከስር በተጠቀሱት ቅመሞቹ ነው፡፡  የሃሳብ ምርጫ፤የስሜቱ ንዝረት፤ንረት፤ግለት፤መንተግተግ፤አዲስነት፤በቋንቋው ጥራትና ምጥቀት፤ቀላልነት በሃረጋቱ ምጣኔ፤በዜማዊነት፤በትኩስነት በአጠቃላይ በቅርጹ በይዘቱ ይወሰናል፡፡

Tuesday, June 5, 2012

ያልተላከው ደብዳቤ


            ያልተላከው ደብዳቤ
እስቲ ወደኋላ በትዝታ ልመልሳችሁ………..መቼም በወጣትነት በተማሪነት ወቅት እንደየ ጊዜና ዘመኑ የማይረሳ ጣፋጭና አስገራሚ የህይወት ገጠመኝ እንደምናሳልፍ እገምታለሁ ወይም ብጠረጥ የሚደንቅ አይመስለኝም፡፡
የኔን  የተማሪነት ዘመን እናውጋ……አንድ ገርል ፍሬንድ እንዲኖርህ ትፈልጋለህ እንበል ቀትታ ሄዶ ማነጋገር ነውር ነው ወይም ደግሞ የሚደፍርም የለም እሷስ ብትሆን ስታናግርህ አይደል……….! እናም እንዴት እንደምታናግራት ሊጨንቅህ ይችላል እናም በወቅቱ በሰፊው የተለመደው ደብዳቤ መጻፍ ነው የፍቅር ደብዳቤ እሱንም ቢሆን አዋቂ፤ምርጥ ጸሀፊ መሆን ይጠይቃል፡፡ማንም ተነስቶ ደብዳቤ አይጽፍም……የወደድካት ልጅ ልቧ እንዲራራ፤ያንተ እንደስትሆን ከፈለክ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ቃላት መምረጥ አለብህ፤ጥቅስ መደርደር፤አባባሎችን መጠቀም ፤አበባ መሳል ፤ልብ ቅርጽ ላይ ጦር ሰክተህ ደም ማንጠባጠብ አለብህ ቢቻል ከደብዳቤው ጋር ደስ የሚል የህንድ ፖስት ካርድ ይሄ ሀሚት አፕ አቻ ከቆንጆ ሚስቱ ጋር ያለበትን ከጀርባው ከ ኤስ  ለ ቲ ብለህ ጽፈህ…… ፡፡ በቃ ምን አለፋህ ጥንቃቄ የተሞላበት ጽሁፍ ካልሆነ የልጅቷን ልብ አራራለሁ ብለህ ጭራሽ ልቧን አምርረኅው ቁጭ ትላለህ፡፡
አንድ የትምህር ቤት ጓደኛ ነበረኝ የፍቅር ደብዳቤ በመጻፍ የሚታወቅ እሱ የጻፈው ደብዳቤ የደረሳት ተፈቃሪ ልቧ የማይራራ የለም እውነት ይገርመኛል ሀሪፍ ጸሃፊ ነው በቃ ፍቅር  ሲይዝህ እሱ ጋር መሄድ ነው፡፡ ከዛ ልክ ሀኪም ዘንድ ወይም አጥፍተህ ዳኛ ዘንድ  እንደቀረበ ጥፋተኛ ትናዘዛለህ ውይም ችግርህን ታወያየዋለህ፡፡
#ምኗን ነው የወደድካት?; ይልሃል ፡፡ በቃ ትንሽ ማፈርህ አይቀርም ትሽኮረመማለህ….ግን ፍቅረኛህን ከማጣት አይበልጥምና ትናገራለህ፡፡ ይገርመኝ የነበረው ይሄ ጓደኛዩ ሲጠይቅህ ኮስተር ብሎ ነው በስሜት ተውጦ ያዳምጥሃል፡፡ አንተም ትናዘዛለህ…………
#እሷን እያየሁ እያሰብኩ ምግብ አልበላ ውሃ አልጠጣ አለኝ አማርኛ ትምህርት አረብኛ ሆነብኝ፤ እሷን ሳይ መራመድ አቃተኝ ትንሽ ጠጠር እንቅፋት እየመታኝ ይህው እግሬ ተላላጠ  
ወዘተ…..; ትነግረዋለህ እሱም አዳምጦህ ሲጨርስ የራሱን ጥበብ መጠበብ ይጀምራል፡፡
(እናንተስ የፍቅር ደብዳቤ ጽፋቹ አታውቁም?)……..                 
                           ! ! !
ደረጀ ፍቅሩ የሚባል ወዳጅ አለኝ መቼም ታውቁታላችሁ (ስርየት) የሚባል ፊልም ደራሲ ነው (ጋጋ) የሚባል አስፈሪ ገጸ ባህሪ የሚተውንበት
#አዲስ አበባ ደበረኝ;
 ሲለኝ ና እለውና ይመጣል ያለሁበት ሀገር እንገባበዛለን ቀዝቀዝ ያለ ቢራ እየጠጣን እንጨዋወታለን የማይነሳ የማይጣል ነገር የለም ሲበዛ ቀልደኛ ነው ጨዋታ ያውቃል የደረስኩትን የተወንኩበትን ፊልሜን እይልኝ አለና ጋበዘኝ በደስታ አየሁት፡፡ በቃ ከዛን ጊዜ በኋላ የአማርኛ ፊልም አይቼ አላውቅም የራሴ ምክንያት አለኝ በቀደም ግን እንዲሁ ከአንድ ወዳጄ ጋር በዚሁ ጉዳይ ስንነጋገር……. (ውይይታችን ይቆይ………. የፍቅር ደብዳቤ በሃገራችን ፊልሞች ግን ልጋብዛችሁ)