ያልተላከው ደብዳቤ
እስቲ ወደኋላ በትዝታ
ልመልሳችሁ………..መቼም በወጣትነት በተማሪነት ወቅት እንደየ ጊዜና ዘመኑ የማይረሳ ጣፋጭና አስገራሚ የህይወት ገጠመኝ እንደምናሳልፍ
እገምታለሁ ወይም ብጠረጥ የሚደንቅ አይመስለኝም፡፡
የኔን የተማሪነት ዘመን እናውጋ……አንድ ገርል ፍሬንድ እንዲኖርህ ትፈልጋለህ እንበል
ቀትታ ሄዶ ማነጋገር ነውር ነው ወይም ደግሞ የሚደፍርም የለም እሷስ ብትሆን ስታናግርህ አይደል……….! እናም እንዴት እንደምታናግራት ሊጨንቅህ ይችላል እናም
በወቅቱ በሰፊው የተለመደው ደብዳቤ መጻፍ ነው የፍቅር ደብዳቤ እሱንም ቢሆን አዋቂ፤ምርጥ ጸሀፊ መሆን ይጠይቃል፡፡ማንም ተነስቶ
ደብዳቤ አይጽፍም……የወደድካት ልጅ ልቧ እንዲራራ፤ያንተ እንደስትሆን ከፈለክ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ቃላት መምረጥ አለብህ፤ጥቅስ መደርደር፤አባባሎችን
መጠቀም ፤አበባ መሳል ፤ልብ ቅርጽ ላይ ጦር ሰክተህ ደም ማንጠባጠብ አለብህ ቢቻል ከደብዳቤው ጋር ደስ የሚል የህንድ ፖስት ካርድ
ይሄ ሀሚት አፕ አቻ ከቆንጆ ሚስቱ ጋር ያለበትን ከጀርባው ከ ኤስ
ለ ቲ ብለህ ጽፈህ…… ፡፡ በቃ ምን አለፋህ ጥንቃቄ የተሞላበት ጽሁፍ ካልሆነ የልጅቷን ልብ አራራለሁ ብለህ ጭራሽ ልቧን
አምርረኅው ቁጭ ትላለህ፡፡
አንድ የትምህር
ቤት ጓደኛ ነበረኝ የፍቅር ደብዳቤ በመጻፍ የሚታወቅ እሱ የጻፈው ደብዳቤ የደረሳት ተፈቃሪ ልቧ የማይራራ የለም እውነት ይገርመኛል
ሀሪፍ ጸሃፊ ነው በቃ ፍቅር ሲይዝህ እሱ ጋር መሄድ ነው፡፡ ከዛ
ልክ ሀኪም ዘንድ ወይም አጥፍተህ ዳኛ ዘንድ እንደቀረበ ጥፋተኛ ትናዘዛለህ
ውይም ችግርህን ታወያየዋለህ፡፡
#ምኗን ነው የወደድካት?; ይልሃል ፡፡ በቃ ትንሽ ማፈርህ አይቀርም ትሽኮረመማለህ….ግን
ፍቅረኛህን ከማጣት አይበልጥምና ትናገራለህ፡፡ ይገርመኝ የነበረው ይሄ ጓደኛዩ ሲጠይቅህ ኮስተር ብሎ ነው በስሜት ተውጦ ያዳምጥሃል፡፡
አንተም ትናዘዛለህ…………
#እሷን እያየሁ እያሰብኩ ምግብ አልበላ ውሃ አልጠጣ አለኝ
አማርኛ ትምህርት አረብኛ ሆነብኝ፤ እሷን ሳይ መራመድ አቃተኝ ትንሽ ጠጠር እንቅፋት እየመታኝ ይህው እግሬ ተላላጠ
ወዘተ…..; ትነግረዋለህ
እሱም አዳምጦህ ሲጨርስ የራሱን ጥበብ መጠበብ ይጀምራል፡፡
(እናንተስ
የፍቅር ደብዳቤ ጽፋቹ አታውቁም?)……..
! ! !
ደረጀ
ፍቅሩ የሚባል ወዳጅ አለኝ መቼም ታውቁታላችሁ (ስርየት) የሚባል ፊልም ደራሲ ነው (ጋጋ) የሚባል አስፈሪ ገጸ ባህሪ የሚተውንበት
#አዲስ
አበባ ደበረኝ;
ሲለኝ ና እለውና ይመጣል ያለሁበት ሀገር እንገባበዛለን ቀዝቀዝ ያለ ቢራ እየጠጣን
እንጨዋወታለን የማይነሳ የማይጣል ነገር የለም ሲበዛ ቀልደኛ ነው ጨዋታ ያውቃል የደረስኩትን የተወንኩበትን ፊልሜን እይልኝ አለና
ጋበዘኝ በደስታ አየሁት፡፡ በቃ ከዛን ጊዜ በኋላ የአማርኛ ፊልም አይቼ አላውቅም የራሴ ምክንያት አለኝ በቀደም ግን እንዲሁ ከአንድ
ወዳጄ ጋር በዚሁ ጉዳይ ስንነጋገር……. (ውይይታችን ይቆይ………. የፍቅር ደብዳቤ በሃገራችን ፊልሞች ግን ልጋብዛችሁ)
© © ©
እጅግ
በጣም ለማከብርሽ ውድ ፍቅረኛዬ ነጺ እንደምን አለሺልኝ ፡፡ እኔ መቼም ታውቂያለሽ…..ካንቺ ሃሳብና ናፍቆት በስተቀር ደህና ነኝ
፡፡ ምን ግን ደህና ነኝ ፍቅርሽ እንደ ፔንዱለም ወዲህ ወድያ ያወዛውዘኛል ይህው ሲርብህ
ይሆንሃል ብለሽ ቋጥረሽ የላክሺልኝ ዳቦ ቆሎ ነክቼው አላውቅም፡፡ በቅጡ ምግብ በልቼ አላውቅም የማስበው አንቺን ብቻ ነው፡፡ በተለይ
ትላንት በደረሰኝ ደብዳቤሽ ላይ እንደነገርሺኝ አደራ ተንከባክበህ አድርሳት ያልኩት ባለ ታክሲው እንዳናደደሽና በጣም
ዘግይቶ እንደመጣ ስትነግሪኝ ንዴቴን መቆጣጠር ነው ያቃተኝ፡፡ ለምንድነው ያናደድካት ብዬ ስጠይቀው እኔ አይደለሁም መካኒኩ
ነው ጉድ የሰራኝ በደንብ መኪናዋን ሳይሰራት ነው አለኝ እኔ ግን አላመንኩም እነዚህ ሹገር
ማሚ እና ሹገር ዳዲ ዎች አጉል ብር አስተምረዋቸው ለጋ ለጋ እንቡጥ እንቡጥ ልጆችን ከያሉበት እያደኑ
ሲያመጡ ነው አንቺን የዘነጉሽ ፡፡ እኔማ ስላንቺ ስል ቢልልኝ ሰማያዊ
ፈረስ ወይም የትሮይ ፈረስ ባዘዝኩልሽ በተመኘሁ፡፡
ነጺዬ
ትላንትና ጓደኛዬ በላይ ደውሎልኝ ነበር ብዙ አወራን ብቸኝነት ከበደኝ ላብድ ነው ሲለኝ እኔ ደግሞ እነዛ የምትለዋውጣቸውን ሴቶች
እየቀያየርክ የትዳር ያለህ ከምትል እንደኔ አንዷን ያዝና ላገባ ነው እያልክ እራስህን ብታሳምን
ይሻላል አልኩት፡፡የኔ ውድ አሁን አሁን ሳስበው እኔና አንቼ ተጋብተን ሀኒሙን የት እንደማሳልፍ መምረጡ
ቸግሮኛል፡፡ለነገሩ አንቺን ሰርፕራዝድ የሚያደርግ ቦታ እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡
ነጺዬ ስላንቺ
እያሰብኩ ከስቻለሁ ጠቁሬያለሁ…. በጣም ናፍቀሺኛል፡፡ አለቃዬ 15 ቀን እንደምቆይ ነግሮኛል እኔ ግን 15ዓመት የሆነ ያህል ነው
የተሰማኝ፡፡ ለነገሩ ከ3 ቀን በኋላ የመምጣት ሰበብ አግኝቻለሁ፡፡ ባለፈው አሜሪካ ያለው ዲያስፖራ አጎቴ መታመሙን ነግሬሽ
ነበር አይደል? አዎ ዛሬ አክስቴ
ደውላ እንደሞተ አረዳቺኝ አዘንኩ….. ስለዚህ አስከሬኑ ወደሃገር ቤት ሲመጣ ለቀብር እመጣለሁ፡፡
ሌላው ይልቅ አክስቴ ያሳሰባት ነገር ልጆቿ ናቸው አንማርም አሉ አለቺኝ ምነው ስላት እኔን እንደናፈቁ
ነገረቺኝ፡፤ ለነገሩ ልክ ናት በጣም ለምደውኛል፡፡ ከት/ቤት መልስ አጫውታቸዋለሁ፡፡
ነጺ በጣም እኮ
ነው የምወድሽ…..አንቺ እኮ ለኔ ብቻ የተፈጠርሽ እንቁ ነሽ ምንም ነገር በመሃላቺን እንዲገባ አልፈልግም በቀደም ገንዘብና
ፍቅር ምን ያገናኘዋል? ስልሽ አንቺ ይሄ የሴቶች ጉዳይ ነው ምን አገባህ ስትይኝ እኔ ደግሞ ይሄማ የወንዶች
ጉዳይ ይስ ለምን አይሆንም?በማለት በክርክር ያሳለፍነው ያባከነው ጊዜ ይቆጨኛል ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ነገር እንደማይደገም ቃል እገባልሻለሁ፡፡
የኔ ውድ ልሰናበትሽ
ነው አሁን ሰዓቱ ከለሊቱ 6 ሰዓት ሆኗል ልተኛ ነው እንደተለመደው መብራት ጠፍቷል እሰራለሁ ያልኩትን መስራት አልቻልኩም አንቺን
ለማስታወስ ግን አራቱን ሻማዎች እዛም እዚም ለኩሻለሁ፡፡ አንቺም ለኔ በ ፌስ ቡክ ፍቅር
ነክ የሆኑ ፖስት አድረጌልሃለሁ ያልሺኝን የፍቅር መግለጫ ካርድ መብራት ሲመጣ አየዋለሁ እስከዛው ግን ከንፈርሺን
ሳሚልኝ፡፤
ያንቺው አደም ሁሴን
i like it
ReplyDeleteadem ምርጥ
ReplyDeleteGood
ReplyDeleteደስ ይላል
ReplyDeleteፍቅር
Deletewow
ReplyDeleteአርፍ
ReplyDelete