የፊደል ጨዋታ ቁ 2
ካቡጊዳ ሰፈር ከኛው ከወንዛችን
የቀዳኀው ወይኑ ይጥም ለጆሮአችን
ብለህ የተየብከው
የግጥም ገነት በር መክፈቻው ቁልፉ ነው….
…. ግና በኔ ሀሳብ ሚስቴ እንዳወቀች
….ሞራልና ድጋፍ ሰቷል ከተባለች
ዋ ብላ ዋ ብላ
ከፊደል ተራ ወጥታ
ታ..ታ..ታ..ታ ያረገችኝ ለታ
መድረሻም የለኝም ከፊደል ገበታ …..አቦ ምርጥ ነው!!!
የቀዳኀው ወይኑ ይጥም ለጆሮአችን
ብለህ የተየብከው
የግጥም ገነት በር መክፈቻው ቁልፉ ነው….
…. ግና በኔ ሀሳብ ሚስቴ እንዳወቀች
….ሞራልና ድጋፍ ሰቷል ከተባለች
ዋ ብላ ዋ ብላ
ከፊደል ተራ ወጥታ
ታ..ታ..ታ..ታ ያረገችኝ ለታ
መድረሻም የለኝም ከፊደል ገበታ …..አቦ ምርጥ ነው!!!
©
© ©
አርአያ መርቲ መካሻ
የፊደል ጨዋታ ቁ 3
ሸ ሸ ሸ ሸ ሸ ሸ ሸ ሸ
ምንም ባቷ ቢመስል በቅቤ የታሸ
አትራፊው እሱ ነው እንዳላየ የሸሸ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
መከራው ብዙ ነው ሲወጡ ተነክሮ
በኋላም ያመጣል ፀፀትና ሮሮ
ቸ ቹ ቺ ቻ
ማን ጥሩ አተረፈ ከከበር ቻቻ
ምነው በቀረብኝ ኖሮ ማለት ብቻ
ተ ቱ ቲ ታ
ምን ሲጨፍር ቢያድር መስሎት ያለው ደስታ
ብዙ ነገር ቢያደርግ በመጠጥ ሞቅታ
ትጠብቀዋለች ፀፀት በሩዋን ከፍታ
ደሞ በተራዋ ደስታ በሯን ዘግታ
ይሄ ነው ምላሼ ለፊደል ጨዋታ፡፡
ምንም ባቷ ቢመስል በቅቤ የታሸ
አትራፊው እሱ ነው እንዳላየ የሸሸ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ
መከራው ብዙ ነው ሲወጡ ተነክሮ
በኋላም ያመጣል ፀፀትና ሮሮ
ቸ ቹ ቺ ቻ
ማን ጥሩ አተረፈ ከከበር ቻቻ
ምነው በቀረብኝ ኖሮ ማለት ብቻ
ተ ቱ ቲ ታ
ምን ሲጨፍር ቢያድር መስሎት ያለው ደስታ
ብዙ ነገር ቢያደርግ በመጠጥ ሞቅታ
ትጠብቀዋለች ፀፀት በሩዋን ከፍታ
ደሞ በተራዋ ደስታ በሯን ዘግታ
ይሄ ነው ምላሼ ለፊደል ጨዋታ፡፡
©
© ©
Mulex peace
ሁለታችሁንም ገጣሚያን
አመሰግናለሁ እንዲህ ነው ስሜት በግጥም ሲገለጽ!!! ለዚህም ነው……………………….
ስነ- ግጥም የረጅም
ጊዜ ታሪክ ያለው ብዙ የህይወት ጉዳዮችን የሚያነሳ የስነ ጽሁፍ ዘርፍ ነው፡፡እንዲሁም የሰው ልጅ ሰው ከሆነበት ቋንቋውን ኪነ -ጥበብ
ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ አኳያ ሲታይ መጀመርያ በድርሰት መልክ የተከሰተ የቋንቋ ጥበብ ነው፡፡እያናዳንዱ ግጥም ጣዕም አለው፡፡ ጣዕሙ የሚለየው ከስር በተጠቀሱት ቅመሞቹ ነው፡፡ የሃሳብ ምርጫ፤የስሜቱ ንዝረት፤ንረት፤ግለት፤መንተግተግ፤አዲስነት፤በቋንቋው ጥራትና ምጥቀት፤ቀላልነት በሃረጋቱ ምጣኔ፤በዜማዊነት፤በትኩስነት በአጠቃላይ በቅርጹ በይዘቱ ይወሰናል፡፡
No comments:
Post a Comment