እንዲህ ነው !
ስነ-ግጥም…የውበት ልቀት ነው
ስነ-ግጥም…….የሰው ልጅ አእምሮ ረቂቅ ውጤት ነው
ስነ-ግጥም …….የራሱ ፍጻሜ አላማ አለው
ስነ-ግጥም……….የስነ ጽሁፍ ፈርጥ ነው፡፡
© © ©
አኩኩሉ……..
ለዚህ ነው በስነ-ግጥም የሰው ልጅ ስሜቱን የሚጭረው ነገር ሲያገኝ የሚያለቅስበት፤የሚስቅበት፤የሚከፋበት፤የሚዝነናበት፤ወዘተ………፡፡ እናም እንደቀልድ ከላይ የገጠምኳትን ግጥሜን ለረጅም ጊዜ ሳጥኔ ውስጥ ቆልፌ በቅርቡ ትንሳዬዋን አግኝታ ለአቅመ ንባብ ስትበቃ በርካታ ገጣሚያን ልብ ውስጥ ገብታ በራሳቸው እይታ የተሰማቸውን ለማለት የበቁት……….፡፡ መቼም ምን ያህል ልቤን አንደነካኝ ቃላት አይፈታውም ! ሁሉንም አመሰግናለሁ ፊት አውራሪ ገጣሚ ዮሃንስ ሞላ ትልቁን ቦታ ይይዛል ከዚህ በኋላም መሰል ግጥሞች ይቀጥላሉ…………እኛም እንጽፋለን !!!! ፡፡
ጨዋታ 1
ላረባት ዶሮ ገዝቼ፣
‘ይጠቅማል’ ቢሉኝ ሰምቼ፣
ፈልፍይ ብዬ ባስታቅፋት፣
እሷ’ቴ ወር አለፋት
ለምን? ብዬ ባስጠይቃት፣
ነፋስ ነው አለች ያጠቃት፣
___የሰፈራት
እኔ ግሙን ታቅፌ፣
‘ዘር አምጣ’ አለች በመርፌ፤
አውራ ጠፋ አሉ ባ’ገሩ፣
ኩኩሉ ‘ሚል በመንደሩ።
/አደም ሁሴን/
ሰኔ 1/1997
ጨዋታ 2
አውራማ ነበር ባገሩ፣
ግን ችግሩ...
ልቡ ሸሽቶ ከመንደሩ፣
መስፈር ጀምሮ ከዱሩ፣
እየመከነበት ዘሩ...
መሸ ነጋ መደንበሩ።
እንዲህም ቢሆን ነገሩ፣
እኛን የጎዳን - መብረሩ፤
ግሙን ታቅፎ መኖሩ።
ላረባት ዶሮ ገዝቼ፣
‘ይጠቅማል’ ቢሉኝ ሰምቼ፣
ፈልፍይ ብዬ ባስታቅፋት፣
እሷ’ቴ ወር አለፋት
ለምን? ብዬ ባስጠይቃት፣
ነፋስ ነው አለች ያጠቃት፣
___የሰፈራት
እኔ ግሙን ታቅፌ፣
‘ዘር አምጣ’ አለች በመርፌ፤
አውራ ጠፋ አሉ ባ’ገሩ፣
ኩኩሉ ‘ሚል በመንደሩ።
/አደም ሁሴን/
ሰኔ 1/1997
ጨዋታ 2
አውራማ ነበር ባገሩ፣
ግን ችግሩ...
ልቡ ሸሽቶ ከመንደሩ፣
መስፈር ጀምሮ ከዱሩ፣
እየመከነበት ዘሩ...
መሸ ነጋ መደንበሩ።
እንዲህም ቢሆን ነገሩ፣
እኛን የጎዳን - መብረሩ፤
ግሙን ታቅፎ መኖሩ።
© © ©
/ዮሐንስ ሞላ/
ግንቦት 15/2004
/ዮሐንስ ሞላ/
ግንቦት 15/2004
አውራ ጠፋ ኡኡታ
አውራ
ጠፋ ኡ ኡ ታ
በርበሬ ቀንጥሱ ድንፋታ
ችግሩ በተባዕት መች ይፈታ
እንስትስ መቼ አረባችሁ
ጥሩ አውራ እሚተካላችሁ
በርበሬ ቀንጥሱ ድንፋታ
ችግሩ በተባዕት መች ይፈታ
እንስትስ መቼ አረባችሁ
ጥሩ አውራ እሚተካላችሁ
© © ©
ኤርሚያስ
ሙሉ
ኤዲያ !.....
ምን አውራ አለና ነው
==አውራ ጠፍቶ ባገሩ:
ስያስካካ የሚውለው
==ሴቱ ሆንዋል በመንደሩ:
አውራማ ድሮ ቀረ
==ያውም አውራ ቢሉ አውራ ዶሮ:
ለጎረቤት የሚተርፍ
==የመንደሩን አስፈልፍሎ:
እንግዲህ ቄቦች ሁሉ
==ምን ይውጣችሁ ይሆን:
ዝምብለው ቢታቀፉት
==ያላውራ ጫጩት አይሆን::
ምን አውራ አለና ነው
==አውራ ጠፍቶ ባገሩ:
ስያስካካ የሚውለው
==ሴቱ ሆንዋል በመንደሩ:
አውራማ ድሮ ቀረ
==ያውም አውራ ቢሉ አውራ ዶሮ:
ለጎረቤት የሚተርፍ
==የመንደሩን አስፈልፍሎ:
እንግዲህ ቄቦች ሁሉ
==ምን ይውጣችሁ ይሆን:
ዝምብለው ቢታቀፉት
==ያላውራ ጫጩት አይሆን::
© © ©
ብቤን ከበደ
esus neber
bayiseber
keandwa sikenif keandwa siber
biyakit enji madaresu
wegu endayiker yelet misu
keandwa sikenif keandwa siber
biyakit enji madaresu
wegu endayiker yelet misu
አንዱአለም መኮንን
doros ale
awira doro ዶሮስ
አለ አውራ ዶሮ
yeteshale kezendiro የተሻለ ከዘንድሮ
chiro yemiyadir yemayidekim ጭሮ የሚያድር የማይደክም
serto asdesach yemayilegim ሰርቶ አስደሳች የማይለግም
tardo enji cherisewit ታርዶ እንጂ ጨርሰውት
lemasfelfel demo chachut ለማስፈልፈል ደግሞ ጫጩት
gorded gorded kinfun zerga ገርደስ ገርደስ ክንፉን ዘርጋ
geref germem eyalagaገ ረፍ ገርመም እያለ
kebuu hula sishkoremem ከቡ ሁላ ሲያሽኮረምም
bilo shulik anigegnim ብሎ ሹልክ አንገናኝም
yeteshale kezendiro የተሻለ ከዘንድሮ
chiro yemiyadir yemayidekim ጭሮ የሚያድር የማይደክም
serto asdesach yemayilegim ሰርቶ አስደሳች የማይለግም
tardo enji cherisewit ታርዶ እንጂ ጨርሰውት
lemasfelfel demo chachut ለማስፈልፈል ደግሞ ጫጩት
gorded gorded kinfun zerga ገርደስ ገርደስ ክንፉን ዘርጋ
geref germem eyalagaገ ረፍ ገርመም እያለ
kebuu hula sishkoremem ከቡ ሁላ ሲያሽኮረምም
bilo shulik anigegnim ብሎ ሹልክ አንገናኝም
አንዱአለም መኮንን
የብሌንን ታሳቢ አድርጌ ጨዋታ 4 ልበለው?
ከአህያና ፈረስ በቅሎን ላበቀላት
የቅይጥ የክልስ የእንግዳ ዘር ጠላት
ይቺ ዶሮ የሚሏት
ከዘሯም እንዲህ ናት ፤
ያላ'ውራ አይሆንላት!
ሲባል ሰማና
አውራ የተባለ፤ ድንጉላ ደፈራት!
'ቢሸግር እኮ ነው' አለ ትግሬ፤ ሃሃሃ…
ከአህያና ፈረስ በቅሎን ላበቀላት
የቅይጥ የክልስ የእንግዳ ዘር ጠላት
ይቺ ዶሮ የሚሏት
ከዘሯም እንዲህ ናት ፤
ያላ'ውራ አይሆንላት!
ሲባል ሰማና
አውራ የተባለ፤ ድንጉላ ደፈራት!
'ቢሸግር እኮ ነው' አለ ትግሬ፤ ሃሃሃ…
© © ©
ምኪን ፑር
አውራ ጠፋ አትበለኝ
ቆፋፍሬ
መሬት ጭሬ
ልበላ……
ሆዴን ልሞላ።
ስውተረተር
ስግተረተር
ሳውካካ
ሳስካካ
ክንፌን አራግፌ
ባጠገቧ አልፌ
ሴቷንም ጎሽሜ
አሳስቄ ስሜ።
እንዲህ እንደደላኝ
ብታየኝ አምሮብኝ
እጅግ ቀናህብኝ
ተንኮል ዘየድክብኝ።
ይታረድ ተባለ ቢላዋ ተሳለ
ውሃ ተቀቅሎ ሽንኩርትም በሰለ።
እናም...
ቢላዋ እንደ ሃብል ካንገቴ አልብሰኸኝ
ዘሬን እያጠፋህ አውራ ጠፋ አትበለኝ።
ቆፋፍሬ
መሬት ጭሬ
ልበላ……
ሆዴን ልሞላ።
ስውተረተር
ስግተረተር
ሳውካካ
ሳስካካ
ክንፌን አራግፌ
ባጠገቧ አልፌ
ሴቷንም ጎሽሜ
አሳስቄ ስሜ።
እንዲህ እንደደላኝ
ብታየኝ አምሮብኝ
እጅግ ቀናህብኝ
ተንኮል ዘየድክብኝ።
ይታረድ ተባለ ቢላዋ ተሳለ
ውሃ ተቀቅሎ ሽንኩርትም በሰለ።
እናም...
ቢላዋ እንደ ሃብል ካንገቴ አልብሰኸኝ
ዘሬን እያጠፋህ አውራ ጠፋ አትበለኝ።
© ©
©
ዳዊት
ኪንግ
አውራ ጠፋ ኡኡታ
አውራ ጠፋ ኡኡታ
በርበሬ ቀንጥሱ ድንፋታ
ችግሩ በተባዕት መች ይፈታ
እንስትስ መቼ አረባችሁ
ጥሩ አውራ እሚተካላችሁ::
በርበሬ ቀንጥሱ ድንፋታ
ችግሩ በተባዕት መች ይፈታ
እንስትስ መቼ አረባችሁ
ጥሩ አውራ እሚተካላችሁ::
© © ©
ኤርሚያስ
ሙሉ
ዴቭ አልተቻልክም
ግን ያ ምክንያት አይህንም
ዝንተ አለም መሞንጨር
አትሞክር ለመብረር
አለምን ለመዞር
እዛው አንድ ቦታ
ስትጭር ስትሞ ነጨር
ከውደ ኋላ መጥተው
በአፍጢምህ ፍንጭር
ግን ያ ምክንያት አይህንም
ዝንተ አለም መሞንጨር
አትሞክር ለመብረር
አለምን ለመዞር
እዛው አንድ ቦታ
ስትጭር ስትሞ ነጨር
ከውደ ኋላ መጥተው
በአፍጢምህ ፍንጭር
© © ©
ኤልሳ
ተገኔ
አውሉማ የ አውራ ዶሮ
ሴቱን አስከትሎ ሲያበላ ነው መሬት ጭሮ
መክቷት ከሌላ ከብሮ አስከብሮ
ተፋልሞ ታግሎ
ጥሎ ወይ አስጥሎ
ወንድነቱን አስመስክሮ
ዘሩን ሊተካ አስፈልፍሎ
ባይሆን እንኳ
ሰፈር መንደሩን ካላስከበረ ሆኖ ታዳሚ
እሱን ብሎ አውራ ዶሮ
የትምሂያጅ ነው ለቃቃሚ::
ሴቱን አስከትሎ ሲያበላ ነው መሬት ጭሮ
መክቷት ከሌላ ከብሮ አስከብሮ
ተፋልሞ ታግሎ
ጥሎ ወይ አስጥሎ
ወንድነቱን አስመስክሮ
ዘሩን ሊተካ አስፈልፍሎ
ባይሆን እንኳ
ሰፈር መንደሩን ካላስከበረ ሆኖ ታዳሚ
እሱን ብሎ አውራ ዶሮ
የትምሂያጅ ነው ለቃቃሚ::
© © ©

