Wednesday, October 10, 2012

ጥቁሩ ክረምቴ


ጎበዝ ሃብታምና ደሃ በሃገሬ እና በመላው ዓለም ልዩነቱ እየሰፋ መሆኑ እየተሰማኝ ነው ወይም የኔ ስሌት ይህን ያመለክታል ፡፡ እዚህ ጋር ቀናነት የህሊና ዳኝነት ትልቁን ሚና ይጫወታል ፍርሃዊ የሃብት ክፍፍል……! ሲባል ቃሉ ቀላል ሊመስል ይችላል ነገሩ ግን ከዛም በላይ ነው፡፡ ለምን ?እንዴት ?ለሚለው ግን በጉዳዩ ላይ ያሉ ሰዎች መልስ የሚሰጡት ነው የሚሆነው፡፡
ወደ ዛሬው ጉዳይ እንምጣ ከዛሬ 13 ዓመት በፊት በአንድ አጋጣሚ በመዲናችን በበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማሩ እትዮÉያዊት አግኝቼ ብዙ አወራን እጅግ ልብ የሚነካ ጨዋታ ተጫወትን…… ቤትና ወላጅ አልባ ሕጻናትን፤ጧዋሪ አልባ አረጋዊያንን ነው የሚንከባከቡት…….፡፡.
ለዚህ
ቀና ተግባር እንዴት ሊነሳሱ እንደቻሉ፤በቀጣይ ምን ሊሰሩ እንዳሰቡ እንዲሁም በዚሁ ሂደት ላይ ሰዋዊ እና ተፈጥሮዋዊ መሰናክሎች እንዴት እንደገጠሟቸው እና ይሄን መሰናክል እንዴት እንዳለፉት በሰፊው አጫወቱኝ፡፡ የበጎ አድራጎት ስራ ሀገሬ ላይ ብዙ እንዳልተለመደና ትኩረት ቢሰጠው ሰው ያለውን እውቀቱን፤ንብረቱን፤ጉልበቱን ለሌለው ፤ለተቸገረ ማካፈልን ቢለምድ ከጥንት የወረስነውን መረዳዳትና መደጋገፍን ባህሉ አድርጎ ቢቀጥል ቢያንስ ሰው ሃገሩን ጥሎ እንደማይወጣ የራበው ጠግቦ እንደሚያድር አጫወቱኝ….፡፡ አቦ ከዚ በላይ ማለት አልችልም ሌላ ቀን ሉላ ቀን እናውራ በዚህ ጉዳይ ሰፊ ጽሁፍ አቀርባለሁ ብዪ ልገምት ለዛሬ በዚሁ ጉዳይ ልቤን ነክቶት የጫርኳት በዚህች ግጥም ተዝናኑ ተወያዩ የዛ ቀን ይበለን ሌላም እንጽለን…….!

አንድ ቃል ነበረ…!!!


ህያው አንድነቶች…!!!


ይህችን ግጥም እጅግ በጣም ለማደንቀው ድምጻዊ ገጣሚና የዜማ ደራሲ ለሆነው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለአዲስ ትዳሩ እንዲሁም በፍቅር አለም ጥንድ ሆነው ለሚኖሩ፤ ተጋብተው…ቤተሰብ ለመሰረቱ ትሆን ዘንድ ፈቀድኩ ከተመቻችሁ ሼር በማድረግ ተገባበዙ መልካም የፍቅር አመት ያድርግልን፡፡

ህላዊ ዳኝነት


Thursday, August 23, 2012

ያልተላከው ደብዳቤ


                        
ይህ ደብዳቤ ከ 15 ዓመት በፊት በቴሌቪዥን በመቶ ሃያ ፕሮግራም ላይ የፍቅር ደብዳቤ ውድድር ላይ ቀርቦ ተሸላሚ የሆነ ነው፡፡ ለትዝታ ይሆናችሁ ዘንድ ለጠፍኩት እንዲህም ደብዳቤ ይፃፍ ነበር እናነተስ የፍቅር ደብዳቤ ተፅፎላችሁ ወይ ፅፋችሁ ታውቃላችሁ?፡፡
                                                     Ø Ø Ø
       አሁን ልክ ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ይመስለኛል……! መጥፎ ለሊት ዮሴፍ አንተ በዚህ ሰዓት ጥሩ እንቅልፍ ላይ እንደሆንክ አልጠራጠርም፡፡ በቃ እኔ ግን አልተኛሁም እንቅልፍን ከረሳሁ ሰነባበትኩ……! የምትናፍቀኝ አንተ ብቻ ነህ ድሮ እንኳን ያቺ ጨረቃ የኔ ትመስለኝ ነበር አሁን አሁን እሷም ርቃኛለች ሀሳቤን ሳልጨርስላት ትታኝ መግባት ጀምራለች፡፡ እናም ብቸኝነት መንፈሴን አብርዶታል የእኔ ውድ ግን ምን ያህል እንደማፈቅርህ ታውቅልኝ ይሆን……….?፡፡ ለህይወቴ ጥበቃ የምትሰጥልኝ ሰው መሆንህን አታውቀውም፤ አንድ ልብ አለን ስንል ለካስ የለንም እኔ ግን በሀሳቤ በፈጠርኩት ሐሳብ በመነሳት አንድ ሐሳብ አንድ ልብ ያለን ነበር የሚመስለኝ፡፡ ስርቅህ እስካይህ እቸኩላለሁ ሳገኝህ ደግሞ ቀና ብዬ እንኳን ለማየት ድፍረቱ የለኝም ፈራለሁ ፍቅር አንዳንዴ ፍረሀት ነው ልበል………….!?፡፡ ዮሴፍ ብዙ እለት ስለአንተ ያጫወትኳትን ጨረቃን ብትጠይቃት ትዘረግፍልሀለች፡፡ ያኔ ገና መፃፀፍ ስንጀምር ታስታውሳለህ……? “ ለሴት እንደኔ ምቹ የለም የሴት አንጀት ነው ያለኝ ሴትን እንደኔ ተንከባካቢም የለም ያልከኝን?፡፡ እኔ ግን እስከዛሬ አልረሳውም የምረሳውም አይመስለኝም ለሴት ልጅ የሚያዝን ሩህሩህ ቡቡ ልብ ያለው ወንድ ገና ከልጅነቴ ተቀርፆብኛል ዮሴፍ ነግሬህ የለ ጨካኝ ወንድ ያስፈራኛል፤ የኔ ውድ አስቴር አወቀን በይበልጥ የወደድኳት በየትኛው ዜማዋ እንደሆነ ታውቃለህ? “ሩህሩህ አዛኝ ነህ ልብል የማይጨክን ራስ ወዳድ ያልሆንክ ለሁሉ የምታዝን ” የሚለውን ሳዳምጥ ነው፡፡ በቃ አንተነትህ ይታየኛል በፊትህ እኮ ግርማ ሞገስ አለህ ገና ሳላይህ እንኳን ቡቡነትህ ሩህሩህነትህ ውስጤን ያተረማመሰው ነበር ዮሴፍ ዛሬማ ልሸሽግህ የምሻው ቅንጣት ነገር የለም ያኔ ስፅፍልህ ምነው አልነገርኩህም? በቃ ሰሰትኩህ ልበል ምናልባት የልቤን ብነግርህ እምትርቀኝ መስሎኝ ሰሰትኩህ፡፡ ደብዳቤህ ሲደርሰኝ ምን ያህል ውስጤ በደስታ እንደሚሞላ ያለኔና ያለ ፈጣሪ ማን ያውቃል ሰው እኮ ያለ ሀሳቡ አይራመድም እንጂ እኔማ ሀሳቤ ጥልቅ ነበር ንፁህ ነበር……..! ጓደኝነታችን የተቃና መልክ ይዞ በአንድ ወቅት ስለአንተ ብቻ ለመንገር ያለምኩት ምስጢር ነው አሁን እምፈታልህ ፡፡ አዎን የኔ ውድ ያለግዜው መንገር ግዴታዬ ሆነ ስለዚህም አድምጠኝ ለአንድ ዓመት ያህል በብዕር ጓደኝነት ቆየን……! እናም ለመገናኘት ቀጠሮ ያዝን በመጀመርያ ሳይህ የወደድኩት ምንህን እንደሆነ ታውቃለህ? ሩህሩህነትን ፊትህ ላይ ለማግኘት ተስገበገብኩ አገኘሁት ግን ሁለመናህ አዛኝነትህን ይመሰክራል ቀናቶች ገፉ በውስጤ እንደያዝኩህ እኔም ቀን ገፋሁ በቀጠሮ መገናኘቱ መጫወቱ በተለይ ደግሞ ስለጥበብ ብዙ መባባሉን ብናፍቀውም ከዚያ በላይ ደግሞ የውስጤ ሀሳብ ልውጣ አልውጣ እያለኝ ይታገለኝ ነበር አላወጣሁትም የኔ ውድ ትላንትና ግን ሁሉን ተረዳሁት በቃ በቅርቡ ጓደኛ እንደተዋወክ ነገርከኝ ላንተ ብስራት መስሎህ መንገርህ ነበር ለእኔ ግን ምፅአት ነው ውስጤ ተተረማመሰ ከዛሬ ከነገ ታውቅልኛለህ ብዬ ሳስብ ሌላ ሰው አወክ……! ግን በጣም ከፋኝ ሰው ሲከፋው አትወድም አይደል? ታዝናለህ ለእኔ ግን ብታዝንም ለውጥ ያለው አይመስለኝም፡፡          ቤት ገብቼ ላለቅስ ሞከርኩ የመከነ ለቅሶ ጨረቃም ያን ቀን አልነበረችም ዮሴፍ ላጣህ እንደማልሻ ልንገርህ አዎን በፍፁም ላጣህ አልፈልግም ባዶነት ይሰማኛል በኔ አስተያየት በኔ ባህሪ ሌላ ሰው መልመድ አይቻለኝም ግን ለካስ “ውሳኔ ማለት ህይወት ነው”፡፡ አዎን ብወስን ኖሮማ ይህ ሁሉ ባልሆነ እኔም ባልተንገላታሁ አንተንም ባላሳዘንኩህ ግን የኔ ሰው ዛሬም የኔ ውድ ብልህ ልክ ነኝ….? አውቀዋለሁ ግን ቢያንስ በልቤ እንድልህ ፍቀድልን፡፡ በቃ ብዙ አልጨቀጭቅህም አፈቅርህ እንደነበር ተረዳልኝ ከአንተም ሌላ በሐሳቤ ሊመጣ የሚችል ሰው ማንም የለም አሁንም አሁንም አልረሳህም፡፡ ዮሴፍ ልጅቷን ወደድካት? አዎን በጣም እንደምትወዳት አስባለሁ ደግሞም ውደዳት እዘንላትም ግን መውደድዋን በውስጧ አምቃ በስቃይ ለተንገላታችው ምስኪን ሰው ትንሽ እዘንላት በቃ ሌላ የምልህ የለኝም አልረሳህም ልተኛ ነው እንዲሁ ለመጋደም መንፈሴን ክፉኛ በርዶታል ግን መኖር ማለት ምንድነው? በቃ ግን እወድሀለሁ፡፡
                                            ያንተው-------

Monday, July 9, 2012

ቴዲ አፍሮ ሰውየውን ለምን ወደደው?


         ቴዲ አፍሮ ሰውየውን ለምን ወደደው?
       

      ድምጻዊ፤ገጣሚና የሙዚቃ ደራሲ የሆነው ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ ለረጅም ጊዜ በተለያየ ምክንያት ከሙዚቃ አልበምና ከመድረክ ስራው ተለይቶ ቆይቶ በቅርቡ #ጥቁር ሰው; በሚለው አዲሱ የሙዚቃ አልበሙ ብቅ በማለት መላውን የሙዚቃ አፍቃሪ በወቅታዊ ብቃቱ መነጋገርያ እስከመሆንና በሙዚቃ አልበሙ ዙርያ የተለያዩ ስሜትና አስተያየቶችን በተለያዩ ጸሃፍትና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መወያያ ርዕስ ሆኖ መሰንበቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
         የዚህ ሙዚቀኛ ጽንፈኛ ደጋፊዎችና በገለልተኛ ሚዛን ባስቀመጡ አድማጮች መካከል በጋዜጣ፤በመጽሄት፤እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ የመረጃ መረብ በነበረ ፍጭት ግጭትና ሚዛናዊና ሚዛን አልባ አስተያየቶችን መቋጫ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤት የሆነውን ቴዲ አፍሮ በወረሃ ግንቦት 28/2004ዓም አዲስ አበባ በሚገኘው ሂልተን ሆቴል # የጥቁር ሰው ; አዲሱ አልበም ምርቃ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይዞ ብቅ ያለው የመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሆነ የሚነገርለት ebs የካሳ ሾው ፕሮግራም ጋዜጠኛ ጋር እንግዳ በመሆን የነበረውን ቆይታ በተደጋጋሚ መመልከታችን፤ማድመጣችን ይታወቃል፡፡ እዚህ ላይ በተለያየ ምክንያት ከቀን ወደቀን በቁጥር እያነሱ የመጡት የግል የህትመት ሚድያዎች ምስጋና ይድረሳቸውና በቴሌቪዥን መስኮት ቃለ ምልልሱን ለማድመጥ እድሉ ላልገጠማቸው የጥበብ አፍቃሪያን የነበረውን ቆይታ እንደወረደ ለህትመት ማቅረባቸውን ከአንድም ሁለት መጽሄትና ጋዜጦች ላይ ለመመልከት ችያለሁ፡፡ ነገም ሌሎች በተለያየ መልክ ሀሳብና ትንታኔ በመስጠት ፤በመተቸት ቢያቀርቡ ተገቢ ነው ብሎ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያምናል፡፡
         የካሳ ሾው አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሳሙኤል ካሳ ዝግጅቱን በማስተዋወቅ የቃለ ምልልሱን የቆይታ መድረክ መጋረጃውን በመክፈት ለድምጻዊው ምስጋና በማቅረብ ቃለ ምልልሱ የሚካሄድበት ቦታ የቴዲ አፍሮ ቤት መሆኑን በመጠቆም ጀመረ፡፡ ይህ ድምጻዊ ከሌላ ቀን በተለየ ሁኔታ በጥቁር ሰው የምረቃ በዓል ላይ ለብሶት የነበረውን በልዩ ሁኔታ ተሰርቶ ያሸበረቀ በሀገር ጥበብ ልብስ ደምቆ የንጉሳዊያን የክብር ዙፋን በሚመስለው ወይም በማይተናነሰው የሶፋ ወንበር ላይ በኩራት፤እግሩን እንዳነባበረ ተቀምጧል:: ከበስተጀርባው በጥሩ የፎቶ ፍሬም የተጠረዘ የግርማዊ ቀዳማዊ ንጉስ ኃይለስላሴ ፎቶግራፍ ይታያል፡፡ በስተቀኝ ግድግዳውን ተደግፎ በልዩ ሁኔታ የተሰራ በመስታወት ያሸበረቀ የእቃ መደርደርያ ውስጡ በተለያየ ጊዜና ወቅት የነበሩ የንጉሳዊያን ዘውድና መጠቀሚያ የመሰሉኝ ጌጣጌጦች በአይነት ተደርድረዋል፡፡ ከዚህ መደርደርያ አለፍ ብሎ ለአዲሱ አልበም መጠርያ የሆኑት የአጼ ምኒሊክ (ጥቁር ሰው) ምስል በቆዳ ላይ ተወጥሮ በእጅ የተሳለ ፎቶግራፍ ከግድግዳው ተሰቅሏል…….! እንዴት ደስ ይላል…….!፡፡
         ቴዲ አፍሮ የጋዜጠኛውን ጥያቄዎች በሙሉ ልብ በተረጋጋና  በሚመስጥ ሁኔታ መመለስ ቀጥሏል…..! ፡፡ የካሳሁን ልጅ ቴዲ……! ከዚህ ቀደም በተለያየ አጋጣሚ በጋዜጣ በመጽሄትና በተለያዩ የመረጃ መረቦች በሙዚቃ ስራዎቹና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ከተለያዩ ጋዜጠኞች ጋር በነበረው ቆይታ ድምጻዊው የሚሰጣቸው መልሶች ለመስማትና ለማንበብ የታደልን የልጁን ግላዊ ስብዕና ጥልቀትና ምጥቀት፤ውስጣዊ ማንነቱን የሙዚቃ ህይወትና ከማህበተሰቡ ጋር ያለውን ጥልቅ ግኑኝነት አውቀን ቆይተናል፡፡ ዛሬ ወቅትና ጊዜያቶች አልፈው አሁን ላይ የደረሰበትን ደረጃ፤አስተውሎት፤ለሚጠየቀው ጥያቄ 'ሚሰጠው መልስ ጥንካሬ…..! ፤ምጥቀትና ቁጥብነት…..! ፤የቃላት ምጣኔ……!፤የሃረጎቹ አሰካክ….!፤እንደው ስሜታዊ ሆንክ ባትሉኝ ነፍስና ስጋ የለበሰ ስልቱን ጠብቆ በዜማ የተቀመረ አንድ የምወደው ወይም የምትወዱት የሙዚቃ ስልት ቃናው እየጣፈጠ ወደማይታወቀው ጥልቅ ሰማየ ሰማያት በመንፈስ የሚያስገባ፤የሚያደርስ ያህል አይነት እየተሰማኝ አደመጥኩት ደጋግሜ ሰማሁት………! ቴዲ ተለውጧል ፡፡ ሚስጥሩ ምን ይሆን……? ፡፡ ወደሌላ የግል አስተያየት ከመግባቴ በፊት ከጋዜጠኛው ጋር በነበረው ቆይታ ከበርካታ አስደናቂ ጥያቄና መልሶቹ መሃል ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝን ክፍል አንብበን እንመለስ፡፡